ሕብረት ባንክ የኮቪድ19 ሥርጭት ለመከላከል አምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

Views: 325

ሕብረት ባንክ የኮቪድ19 ሥርጭትን ለመከላከል የአምሥት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ድጋፉም የቫይረሱን ሥርጭትት ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት የሚውል እንደሆነ ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ ላይ ገለጸ።

ለጤና ሚንስትር አምስት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረገው ባንኩ፣ በዚህ ብቻ እንደማይቆምና ቫይረሱን ለመግታት ከሚሰሩት ባለድርሻ አካላት ጋር ቀጣይነት ያለው ሥራ እንደሚሰራም ገልጿል።

ባንኩ ጨምሮም፣ ደንበኞቹ ከቫይረሱ እራሳቸውን እንዲከላከሉ ባንክ ድረስ መምጣት ሳይጠብቅባቸው የኤሌክትሮኒክስ ባንክ፣የኦንላይን እንዲሁም የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት እንዲጠቀሙም አሳስቧል።

 

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com