ማራቶን ሞተር በኮሮና ምክንያት የኤሌክትሪክ መኪናውን ለገበያ አያቀርብም

Views: 258

የኮሪያው የመኪና አምራች ሀይዉንዳይ ምርቶችን በኢትዮጵያ የሚገጣጥመው ማራቶን ሞተር በሚያዚያ ወር ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ መኪኖችን ለገበያ የማቅረብ ሐሳቡን በኮሮና ምክንያት መሰረዙን አስታወቀ።

ማራቶን ለአዲስ ማለዳ በላከው መግለጫ ላይ እንደገለፀው ይህ መኪና የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ መኪና በመሆኑ እና የሚመረቀውም በሰፊ ዝግጅት በመሆኑ ምክንያት ነው እንዲሰረዝ የተደረገው። ምርቃቱ ሳይካሄድ ለገበያ መቅረብ ስለሌበት ላልተወሰነ ጊዜ አዘግይተነዋል፤ ለዚህም ደንበኞቻችን ይቅርታ እንጠይቃለን ሲሉ የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መልካሙ አሰፋ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

በቤት ውስጥ በሚገኝ የኤሌክትሪክ ኃይል ይሞላሉ ተብለው የነበሩት እነዚህ መኪኖች ከሚመጡበት አገር ሲጓዙ እስከ 250 በመቶ ድረስ የዋጋ ጭማሪ ቢኖራቸውም፣ ወደ አገር ሲገቡ ግን ኤክሳይስ ታክስን ጨምሮ የተለያዩ ክፍያዎች ስለተነሱ ዋጋው ተመጣጣኝ እንደሚሆንም ድርጅቱ አስታውቆ ነበር።

በተጨማሪም የአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የሆነው ድርጅቱ፣ መንግሥት የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝን ለመከላከል ለሚያደርገው ጥረት የአንድ ነጥብ ኹለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉንም መልካሙ ጨምረው ገልፀዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 73 መጋቢት 19 2012

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *

This site is protected by wp-copyrightpro.com