10ቱ ኦስካር ያሸነፉ ጥቁር አሜሪካዊ የፊልም ባለሞያዎች

0
807

ምንጭ፡- ባዮግራፊ (2021)

በ12ኛው የአካዳሚ አዋርድ ላይ ነበር፣ በአውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ1940። በኦስካር ታሪክ የመጀመሪያ ጥቁር አሜሪካዊት በምርጥ ረዳት ተዋናይነት አሸናፊ ሆነች። ፊልሙ ‹Gone with the wind› የሚል ርዕስ ያለው ሲሆን፣ በረዳት ተዋናይነት ያሸነፈችው ሄይቲ ማክዳንኤል ናት። አሸናፊዋ ታድያ ግን በፊልሙ ዳይሬክተር ጥረት ባይሆን ኖሮ በመድረኩ ንግግር እንድታደረግ ፈቃድ አልነበራትም፤ ምክንያቱም ብዙ ነጭ የፊልም ባለሞያዎች የታደሙበት አዳራሽ ነው። ነገር ግን ወጥታ አጭር ንግግር የምታገኝበትን እድል አገኘች።
ከእርሷ በመቀጠል በ1964 በምርጥ ረዳት ተዋናይነት ያሸነፈው ሲድኒ ፖይቲየርም የዘረኝነቱ ማዕበል ባላረፈበት ወቅት ነበር ‹Lilies of the field› በተሰኘ ፊልም ሽልማቱን የተቀበለው። ያም ለዘረኞች የሚሆን ወሬ አላጣውም። ሽልማቱን የሰጠችው አና ባንክሮፍት የተባለች ተዋናይት ‹እንኳን ደስ አለህ!› ብላ ጉንጩን ስማዋለች። ይህም ለብዙ ዘረኞች ‹አሳፋሪ› ድርጊት ሆኖ ነበር። ኦስካር አሁንም ከዚህ ዘረኝነት የወጣ አይመስልም። በየዓመቱም ቅሬታዎች እንደተነሱበት ነው። እስካለፈው ዓመት 2021 ድረስ በኦስካር የ93 ዓመት ታሪክ፣ በድመሩ 20 ጥቁር አሜሪካውያን ብቻ ናቸው በተለያየ ዘርፍ ሽልማቱን ያገኙት።


ቅጽ 4 ቁጥር 178 መጋቢት 24 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here