የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ሹመት ፀደቀ

0
870

ሐሙስ መጋቢት 29 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሥራ አመራር ቦርድ ዘጠኝ አባላት ሹመት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፀደቀ።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ እያካሄደ ባለው ስብሰባ በቀዳሚነት የምክር ቤቱን 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለጉባኤ መርምሮ አፀድቋል፡፡

በማስከተልም ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንን ለማቋቋም በወጣው አዋጅ ቁጥር 1238/2ዐ13 መሠረት ለባለስልጣኑ የሥራ አመራር ቦርድ በዕጩነት የቀረቡትን አባላትን ሹመት በሕዝብ ተወካዮች አባላት ውይይት ተደርጎበት አፅድቋል።

በዚህም መሰረት፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የሥራ አመራር ቦርድ አባላት እጩ ሆነው የቀረቡት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን (የቦርዱ ሰብሳቢ)፣ አምባሳደር ናሲሌ ጫሊ (የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ)፣ አምባሳደር ሀሰን ኢብራሂም (አባል)፣ ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ (አባል)፣ ዶ/ር በድሉ ዋቅጅራ (አባል)፣ ዶ/ር መሳይ ገብረማርያም (አባል)፣ዶ/ር ወዳጄነህ መሃረነ (አባል)፣ ቀሲስ ታጋይ ታደለ (አባል እንዲሁም ኡስታዝ ያሲን ኑሩ (አባል) በመሆን ሹመታቸው ፀድቀዋል።

ሹመቱም በውሳኔ ቁጥር 8/2ዐ14 በ11 ተቃውሞ እና በ17 ድምፀ ታአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here