10 ነዳጅ በቅናሽ ዋጋ የሚገኝባቸው አገራት

0
1122

ምንጭ፡- ኢቫንስ ሀልሻው (2021)

የነዳጅ ዋጋ በተለያየ ምክንያት ደጋግሞ ለውጦችን ያሳያል። በዚህ የዋጋ ለውጥ ውሰጥ ግን የዋጋ መጨመር እንጂ መቀነስ ተሰምቶ አያውቅም። አንዳንድ አገራት ታድያ፣ ነዳጅ ከሚገመተው በላይ ዋጋው ዝቅ ያለ ሊሆን ይችላል። ኢቫንስ ሀልሻው የተባለ ገጽ ግሎባል-ፔትሮል-ፕራይዝን ጠቅሶ ባስነበበው ዘገባና ባወጣው ዝርዝር፣ ቬንዝዌላ ነዳጅ በርካሽ ዋጋ ከሚገኝባቸው አገራት መካከል ቀዳሚ ናት። ቬንዝዌላን ጨምሮ ተከታዮቹ ዘጠኝ አገራትም፣ በዓለማችን ትልልቅ የነዳጅ ማከማቻ ዴፖ ጭምር የሚገኝባቸው ናቸው። ይህም ነው የነዳጅ ዋጋ በእነዚህ አገራት እንዲቀንስ ያስቻለው።
በዐስርቱ ዝርዝር ዐስረኛ ላይ የተቀመጠችው አፍሪካዊቷ ናይጄሪያ ናት። አንጎላ እና አልጄሪያም በዝርዝሩ ተካትተዋል። ጎረቤታችን ሱዳን ስድስተኛ ስትሆን አንዱ ሊትር 15 ብር ገደማ ነው፡፡


ቅጽ 4 ቁጥር 179 ሚያዝያ 1 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here