የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር አዲስ ሊቀመንበር መምረጡን አስታወቀ

0
835

የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር (The Ethiopian Reinsurance S.C) በቅርቡ አዲስ ሊቀመንበር እንዲሁም ምክትል ሊቀመንበር መምረጡን ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር ዘጠኝ የቦርድ አባላትን መርጦ በብሔራዊ ባንክ ከጸደቀለት በኋላ፣ አዲስ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር በመረጠበት ወቅት መሠረት በዛብህ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸውን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። መሠረት በዛብህ የሕብረት ኢንሹራንስ ዋና ሥራ አስፈፃሚም ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።
ማክሰኞ፣ ሚያዚያ 04/2014 በኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር ቢሮ ሊቀመንበር እና ምክትል ሊቀመንበር ለመምረጥ በተካሄደ ስብሰባ መሰረት ሊቀመንበር (Chairperson) ሆነው መመረጣቸውን አረጋግጠው፣ ነጻነት ለሜሳ ደግሞ ምክትል ሊቀመንበር (Vice chairperson) ሆነው እንደተመረጡ ተናግረዋል።
እንደ ሊቀመንበሯ ገለጻ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቸኛ የሆነው የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር ከተመሠረተ አምስት ዓመት ሆኖታል። ባንኮች እና አክሲዮን ኩባንያዎች በየሦስት ዓመቱ ሊቀመንበር መምረጥ ስላለባቸውም፣ የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበርም በቅርቡ ያካሄደው የሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበር ምርጫ ለሦስተኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል።
የኢትዮጵያ ጠለፋ መድን አክሲዮን ማኅበር ባለአክሲዮን ኩባንያዎችን አባል አድርጎ፣ የጠለፋ ዋስትና አገልግሎትን የሚሰጥ ነው።


ቅጽ 4 ቁጥር 180 ሚያዝያ 8 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here