ከፍተኛ የደም እጥረት ማጋጠሙን ብሔራዊ ደም ባንክ ይፋ አደረገ

0
431

በመላ ኢትዮጵያ ከፍተኛ የደም እጥረት መከሰቱን ብሔራዊ ደም ባንክ ያልታወቀ ሲሆን፣ በአገሪቱ ያለውም አጠቃላይ የመጠባበቂያ ደም ክምችት ከአምስት ቀናት የማይዘል መሆኑንም አሳውቋል::
በብሔራዊ ደም ባንክ አገልግሎት ሠሞኑን ስለደም እጥረቱ በተናገሩበት ወቅት እንደገለፁት፤ በአገሪቱ ያሉት የኹለቱ ትላልቅ ሃይማኖቶች ተከታዮች ፆም ላይ መሆናቸውን ተከትሎ በመላ አገሪቱ ከፍተኛ የደም እጥረት ተከስቷል:: በአገሪቱ ያለውም የመጠባበቂያ ደም ክምችት ከአምስት ቀናት የማይበልጥ ነው ሲሉ የእጥረቱን አሳሳቢነት ይፋ አድርገዋል::
በአገር ደረጃ ሲታይ ከፆም በፊት በዚህ ዓመት የነበረው የደም ክምችት አመርቂ የሆነበት ዓመት ነበር ብሎ መውሰድ ይቻላል ያለው ተቋሙ፤ የዐቢይ እና ረመዳን አጽዋማት ከገቡ በኋላ የመደበኛ ደም ለጋሾችም ሆነ ሌሎች ለጋሾች ቁጥር በከፍተኛ መጠን ማሽቆልቆሉን አሳውቀዋል::
የፆም ወቅቱ የደም ክምችት ላይ ከፍተኛ እጥረት እንደፈጠረ የተነገረ ሲሆን፣ በተለይ እንደ ፕላትሌት የደም ተዋፅዖ እና ‘ኦ’ የደም ዓይነት ክምችቶች እጥረት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ተብሏል:: ፕላትሌት የሚባለው የደም ተዋፅዖ ለካንሰር ታማሚዎችና የደም መፍሰስ ችግር ላለባቸው ታካሚዎች የሚሰጥ የደም ዓይነት ነው።


ቅጽ 4 ቁጥር 181 ሚያዝያ 15 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here