መነሻ ገጽዜናየእለት ዜና“ጽንፈኝነት የሰው ልጆች ጸር ነው” በሚል መሪ ቃል በሰበታ ከተማ ውይይት እየተካሄደ...

“ጽንፈኝነት የሰው ልጆች ጸር ነው” በሚል መሪ ቃል በሰበታ ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው

ዕረቡ ሚያዚያ 26 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) “ጽንፈኝነት የሰው ልጆች ጸር ነው” በሚል መሪ ቃል በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት በሰበታ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በውይይት መድረኩ ላይ ከ1ሺህ 300 የሚበልጡ የከተማዋ ወጣቶች፣ ምሁራን እና የንግዱ ማኅበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈውበታል።

የሰበታ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አልፊያ አብዱረህማን የውይይቱ ዋና ዓላማ ወጣቶች በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማስቻልና በአገራዊ ሠላምና ጸጥታ ማስከበር ሥራ ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ ማድረግ ነው ብለዋል።

የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ሃብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር) ወጣቶቹን፣ ምሁራኑን እና የንግዱን ማኅበረሰብ ተወካዮች ያወያዩ ሲሆን ሀገራዊ ለውጡን ከማረጋገጥ ረገድ ወጣቶች በነበራቸው ሚና፣ ከለውጡ ጋር ተያይዞ እየታዩ ባሉ ተግዳሮቶችና በወቅታዊ አገራዊ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የመወያያ ጽሑፍ አቅርበዋል።

በቀረበው የመነሻ ጽሑፍ ላይም ውይይት እንደሚካሄድ የኦቢኤን ዘገባ አመላክቷል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

 

 

 

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች