ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ሥምምነት ፈረመ

0
663

ሰኞ ግንቦት 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ዓለም ባንክ በኢትዮጵያ በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር (300 ሚሊዮን ዶላር) ድጋፍ ለማድረግ ከገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ሥምምነት ተፈራረሙ።

ሥምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ከኢትዮጵያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና የኤርትራ ዳይሬክተር ኦስማኔ ዶኔ ጋር ተፈራርመዋል።

የድጋፍ ሥምምነቱ በጦርነቱ በአማራ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በግጭት የተጎዱ አካባቢዎችና ማህበረሰብ ለመልሶ ግንባታና መልሶ ማቋቋም ሥራዎችን በአስቸኳይ ለመደግፍ ያለመ ነው መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

ድጋፉ በተመረጡ የግጭት ተጎጂ ወረዳዎች የጤና፣ የትምህርትና የውሃ መሰረት ልማት መዘርጋት ብሎም ለፆታዊ ጥቃት የተጋለጡ ሴቶችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም ይውላል ተብሏል።

የፌዴራል መንግስት በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ለመገንባት በተያያዘው ዓመት 5 ቢሊየን ብር መመደቡን ያስታወሱት የገንዘብ ሚኒስትሩ፤ በቀጣይ በጀት ዓመት ደግሞ 20 ቢሊዮን ብር መመደቡን ገልፀዋል።

የዓለም ባንክ ለመልሶ ግንባታ የሚውል ፕሮጀክት ያደረገው የልማት ፋይናንስ ድጋፍ በጦርነቱ ከደረሰው ውድመት አንፃር ከፍተኛ ባይሆንም ለተጎዱ አካባቢዎች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ግን ትልቅ ፋይዳ እንደማኖረው ገልፀዋል።

የዓለም ባንክ ድጋፍ በጦርነቱ በድርቅ፣ በኮቪድ-19ና በዓለም አቀፍ ክስተት የተጎዳውን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለማገዝ ጉልህ ሚና እንደሚኖረውም ጠቅሰዋል።

_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here