በዓለም የፕሬስ ነጻነት መጠቆሚያ ኢትዮጵያ 110ኛ ደረጃን ይዛለች

0
500

ከትላንት በስቲያ ይፋ በሆነው እና ‘ሪፖርተርስ ዊዛውት ቦርደርስ’ በሚያዘጋጀው ዓመታዊው የፕሬስ ነጻነት ደረጃ መጠቆሚያ መሠረት ኢትዮጵያ ከአምናው አንፃር 40 ደረጃዎችን በማሻሻል 110ኛ ደረጃን ይዛለች። መጠቆሚያው ኢትዮጵያ ደረጃዋን ለማሻሻል ያበቃት የታሰሩ ጋዜጠኞችን እና ጦማሪዎችን መልቀቋ፣ የታገዱ ድረገጾችን መክፈቷ እና አፋኝ አዋጆችን ለማሻሻል ሥራ መጀመሯ እንደሆነ ገልጿል። ይሁን እንጂ የኢንተርኔት በተደጋጋሚ መቋረጥ ለጋዜጠኞች አንዳንድ ዜናዎችን ለመሥራትና ከዜና ምንጮቻቸው መገናኘት እንቅፋት እንደሆነባቸው ጠቅሷል። ኖርዌይ፣ ፊንላንድ እና ስዊድን በመጠቆሚያው ቁንጮ ላይ የተመደቡ አገራት ሆነዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 24 ሚያዚያ 12 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here