ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍትሕ አካላት ጋር ውይይት አደረጉ

0
604

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍትሕ አካላት ጋር ውይይት አደረጉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሙስ፣ ግንቦት 29 ከመላው አገሪቱ ከተወጣጡ የፍትሕ አካላት ጋር ውይይት በጽሕፈት ቤታቸው ውይይት አድርገዋል። መድረኩ የፍትሕ ሥርዓቱን ለውጥና የማሻሻያ ሥራዎች ላይ ትኩረት ማድረጉ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ባለፈው ዓመት በዘርፉ የተካሔዱ የሕግ ማሻሻያዎች መሠረታቸውን በተቋማት ላይ ትኩረት ማድረግ ያለባቸው ሲሆን አቅምን የመገንባትንና የመንግሥት ኀላፊዎችን ጨምሮ በሕግ የበላይነት የሚያምን ማኅበረሰብ የመፍጠር አስፈላጊነት ላይ አተኩረዋል። ከዚህ ባለፈም የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ መደበኛ ያልሆኑ ማኅበራዊ ዕሴቶቻችንን ሚና የጠቀሱት ሲሆን ሞራላዊ በሆነ መንገድ ኀላፊነትን መወጣት እና ሞራላዊ በሆነ መንገድ በማለም መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት እንደሚገባ በማለት ገልጸዋል።

የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ከሞራላዊ ግዴታ በተጨማሪ ሞራላዊ መነሳሳትን ለማበልጸግና ለማሳደግ መሥራት እንደሚያስፈልግ የጠቀሱት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አስተዳደራቸውም በፍትሕ ሥራ ላይ ጣልቃ እንደማይገባ ተናግረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 31 ሰኔ 1 ቀን 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here