በኹለት ወር ውስጥ የ5 ሺሕ መኪኖች ፍጥነት ይገደባል

0
579

የፌደራል የትራንስፖርት ባለሥልጣን በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገውን የፍጥነት መገደቢያ ማሽን እስከ መስከረም መጨረሻ ለ5 ሺሕ የንግድ መኪኖች እንደሚገጥም አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ ባሳለፍነው ሳምንት የመጀመሪያ ዙር የፍጥነት መገደቢያ ለናሙና በ10 መኪኞች ላይ የገጠመ ሲሆን ፍቃድ በተሰጣቸው 4 ኩባንያዎች አማካኝነት በአገሪቱ ለሚገኙ መኪኖች እንደሚገቡ ታውቋል።

የፍጥነት መገደቢያ ማሽኑ ማንዋል እና አውቶማቲክ ሲስተም ላላቸው መኪኖች የሚያገለግል ሲሆን በመኪኖቹ የውስጠኛው የፊት ክፍል ላይ ይገጠማል። በዚህ ማሽን አማካኝነት መኪኖቹ ያሉበትን ቦታ እና የሚጓዙበትን ፍጥነት መለየት ያስችላል።በዚህም መሰረት የመኪኖቹን የ72 ሰዓታት እንቅስቃሴ ለማወቅ ያስችላል።

በተጨማሪም ማሽኑ “ባር ኮድ” ያለው በመሆኑ ሊያገለግል የሚችለው ለአንድ መኪና ብቻ ነው። ስለውጤታማነቱ ኬንያ ማሽኑን ተግባራዊ በማድረግ ከፍጥነት ጋር ተይይዞ የሚደርሱ አደጋዎችን በ30 በመቶ መቀነስ መቻሏን የመንገድ ትራፊክ ደኅንነት ዳይሬክተር ያዕቆብ በላይ አስረድተዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 40 ነሐሴ 4 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here