10ቱ ብዙ ሴት የሕዝብ ተወካዮች ያላቸው አገራት

0
557

ምንጭ: ዊፎረም ድህረ ገፅ

ባሳለፍነው ሳምንት ከአቅም በላይ በሆነ ችግር ልጃቸውን ወደ ህዝብ ተወካዮች አዳራሽ ይዘው የገቡት እና ከምክር ቤቱም እንዲወጡ የተደረጉት የ ዙለይካ ሃሰን ሃገር ኬኒያ ካሏት መቀመጫዎች ውስጥ 21.8 በመቶ የሚሆነው መቀመጫ በሴት ተወካዮች የተያዘ ነው፡፡

በአለም ላይ ለረጅም አመታት ያለማቋጥ በተደረጉ ከፍተኛ ጥረቶች የሴቶች ውክልና እያደገ ቢመጣም አሁንም ሴቶች በተለይም በፖለቲካው ዘርፍ ያላቸው ተሳትፎ አሁንም ከፍተኛ ክፍተት የሚታይበት ነው፡፡ ይህም በተለይ ሴቶች ያለባቸው ባህላዊ ጫና እንዲሁም የትምሀርት እድል እጦት ዋናኛ ምክኒያት መሆናቸው ይነሳል፡፡

በአለም ላይ የፆታ ክፍተትን ካጠበቡ ሃገራት መካከል በስድስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው አፍሪካዊቷ ሃገር ሩዋንዳ በሴት ተወካዮችም ቁጥር ቁንጮ ላይ ትገኛለች፡፡ በዝርዝሩም ናሚቢያ እና ደቡብ አረፍሪካ ከብዙ ምእራባዊያን ሃገራት በተሻለ የሴቶችን ውክልና በህግ አውጪዉ ውስጥ ያረጋገጡ ሲሆኑ አሜሪካ በዚህ ረገድ 23.5 በመቶ የሚሆኑት የህዝብ ተወካዮቿ ሴቶች በመሆናቸው በ75ኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡

ኢትጵያም 39 በመቶ የሚሆነው የምክር ቤት መቀመጫዋ በሴቶች የተያዘ ሲሆን በ2002ቱ ምርጫ የ27.8 በመቶ መቀመጫ በሴቶች የተያዘ ነበር፡፡ ውክልናው በ1992 ከነበረበት 7.7 መበቶ በ1997 ከፍተኛ እድገት በማሳየት ወደ 21.4 በመቶ ከፍ ብሎም ነበር፡፡

ቅጽ 1 ቁጥር 40 ነሐሴ 4 2011

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here