10ቱ የአልኮል መጠጦች በከፍተኛ ደረጃ የሚጠጣባቸው የአፍሪካ አገራት

0
502

ምንጭ:ሔሊኮፕሪቪው (helicopterview) 2018 (እ.ኤ.አ.)

ከሰሞኑ በዓል በመሆን ከምግቡ እንዲሁም ከመጠጡ ብሉልኝ ጠጡልኝ እየተባባሉ የሚገባበዙበትም ነው። ታድያ በቤት ውስጥ የሚዘጋጀውን እንዲሁም ከገበያ የሚገኘው የአልኮል መጠጥ በየቤቱ መገኘቱ አይቀርም። ትሬዲንግ ኢኮኖሚክስ የተባለ ድረገጽ የኢትዮጵያውያን የአልኮል መጠን ተጠቃሚነት በነፍስ ወከፍ 4.3 እንደሆነ ዘግቧል።

ይህን በአንደኝነት ደረጃ ካለችው ናይጄሪያ ጋር ሲተያይ ከእጥፍ በላይ የሚያንስ ነው። ዩጋንዳ እና ኬንያ በተከታታይነት ብዙ የአልኮል መጠን በመጠቀም ሥማቸው ይገኛል። በአንጻሩ ከፍተኛ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከልም በአንጻራዊነት ቦትስዋና እና ታንዛንያ ይገኛሉ።

በአንጻሩ ግብጽ እና ኒጀር በተመሳሳይ 0.3 ሊትር፣ እንዲሁም ሊብያ ምንም በሚባል ደረጃ የአልኮል መጠጦችን ባለመጠቀም በዝቅተኛ የአልኮል ተጠቃሚዎች ሰንጠረዥ ተቀምጠዋል።

በዓለም ደረጃ ምሥራቅ አውሮፓ የሚገኙት ሞልዶቫ እንዲሁም ቤላሩስ ከፍተኛ የአልኮል መጠንን በነፍስ ወከፍ በመጠቀም የዓለምን ሰንጠረዥ ከላይ ሆነው እየመሩት ነው።

ቅጽ 1 ቁጥር 44 ጳጉሜ 2 2011

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here