ኢትዮጵያ የኒውዚላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቀረበች

0
634

የኒውዚላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በወተት ልማት እና ተዋጽኦ ዘርፍ ተሰማርተው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ አቅርቧል። የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዲኤታ ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) በኒውዚላንድ አቻቸው የተመራውን ልዑካን ቡድን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸው ወቅት ኢትዮጵያ ከኒውዚላንድ ጋር በአየር ንብረት ለውጥ፣ በኢንቨስትመንት፣ በምጣኔ ሀብት እና ሴቶችን በማብቃት ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ፅኑ ፍላጎት እንዳላት ሚኒስትር ዲኤታ ማርቆስ አስታውቀዋል። ማርቆስ አያይዘውም የኒውዚላንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በወተት ልማት ዙሪያ ቢሳተፉ ከአፍሪካ እና ከመካከለኛው ምስራቅ በኩል ካለው ከፍተኛ የገበያ ፍላጎት የተነሳ ተጠቃሚ ሊሆኑ እንደሚችሉም አስገንዝበዋል።

የነውዚላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ፍሌቸር ቲባቱ እንደተናገሩትም ኢትዮጵያ በሰላም ግንባታ ዙሪያ እያደረገች ያለው ተግባር የሚደነቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ጨምረውም ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት ቀዳሚዋ የኒውዚላንድ ምርጫ እንደሆነችም ጠቁመዋል። ኒውዚላንድ ለኢትዮጵያ በግብርና፣ በታዳሽ ኃይል፣ እንዲሁም በእውቀት ሽግግር ዘርፍ ድጋፍ እንደምታደርግም ቃል ገብተዋል። በመጨረሻም ኒውዚላንድ አዲስ የኢምባሲዋን ቅጥር  እንደምትከፍትም አስታውቀው በ2006 ጊዜያዊ ኢምባሲ በአዲስ አበባ መከፈቱንም አውስተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here