ሊባኖሳዊው ግለሰብ በቦሌ አየር ማረፊያ ”ታግተው” ተወሰዱ

0
759

ሐሰን ጃበር የተባሉ ሊባኖሳዊ የንግድ ሰው በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀናት ትራንዚት  በሚያደርጉበት አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ታግተው እንደተወሰዱ እና የደረሱበት እንዳልታወቀ ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል። በዕለቱ ከአፍሪካዊቷ አገር ጋቦን በመነሳት በአዲስ አበባ አድርገው ወደ ሊባኖስ ቤሩት በማምራት ላይ የነበሩት ሐሰን አዲስ አበባ ደርሰው ቀጣዩ ጉዟቸውን ለማድረግ በሚሰናዱበት ወቅት ለጊዜው ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ዕገታ እንደተፈፀመባቸው እና ሊሰወሩ እንደቻሉ የተገለፀው። የግለሰቡ ቤተሰቦች ከሊባኖስ ጋዜጣ አል አክበር ጋር ባደረጉት ቆይታ ከዕገታው ጀርባ የእስራኤል የስለላ ድርጅት ሞሳድ እንደሚኖር ጥርጣሬያቸውን ገልፀዋል።

 

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ግለሰቡ ከዓመታት በፊት በፈረንጆች 2017 ከሒዝቦላህ ጋር ግንኙነት አለው በሚል በጋቦን የፀጥታ አካላት ምርመራ የተደረገባቸው መሆኑን አውስቷል። ይሁን እንጂ ሐሰን ከሒዝቦላህ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።

በአሁኑ ሰዓት ሊባኖሳዊው ግለሰብ የት እና በምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ የሚታወቅ ነገር የለም።

ስለጉዳዩ ኢትዮጵያ አየር መንገድ ምንም የሚያውቀው ነገር አለመኖሩን ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

የሊባኖስ የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኢትዮጵያ በኩል የሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት በጉዳዩ ላይ ግልፅ ምላሽ እስከ መጪው ሰኞ መስከረም 5/2012 ድረስ እንዲሰጥበት አሳስበዋል። ካልሆነ ግን ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የሊባኖስ መንግስት አስጠንቅቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here