10 በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ያሏቸው አገራት

0
1070

ምንጭ፡- ቤዚክ ፕላኔት (2021)

ወጣትና ወደ ሥራ ለመሰማራት በእውቀትም በአቅምም ዝግጁ የሆነ ትውልድ የሚወጣው ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ወይም ከዩኒቨርሲቲዎች እንደሆነ ይታመናል። ለዚህም ነው አገራት በጥራትም በብዛትም ዩኒቨርሲቲዎች ላይ ለመሥራት ደፋ ቀና የሚሉት። በተለይ ትምህርትን ከመደበኛና አንደኛ ደረጃ ጀምሮ የማስፋፋት ሥራ በሚሠራባቸው እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አዳጊ አገራት፣ ከፍ ብለው ወደ መሰናዶ የሚገቡና ዩኒቨርሲቲ ለመግባት የሚጠባበቁ ተማሪዎች ስለሚበረክቱ፣ የዩኒቨርሲቲዎች በስፋት መከፈት ወሳኝ ነው፤ ጥራታቸውን አብሮ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑ ሳይዘነጋ!
ታድያ በዩኒቨርሲቲዎች ሕንድ ከዓለማችን በአንደኛነት ተቀምጣ ትገኛለች። በተከታይነት አሜሪካ እና አርጀንቲና ሲገኙ፤ ቻይና በ10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ታድያ እነዚህ ዩኒቨርሲቲዎች የአገሬው ተወላጅ የሆነን ተማሪ ብቻ ሳይሆን የውጭ ዜጋንም ጭምር የሚያስተናግዱና በነጻ የትምህርት እድል ብዙዎችን ለመቀበል በየጊዜው በራቸውን ከፍተው የሚጣሩ ናቸው።


ቅጽ 4 ቁጥር 183 ሚያዝያ 29 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here