አል-ሸባብ በድንበር አከባቢ የቀበረው በርካታ የጦር መሳሪያ በቁጥጥር ሥር ዋለ

0
1558

ማክሰኞ ግንቦት 2 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) አሸባሪው አል-ሸባብ በድንበር አካባቢ የቀበረው በርካታ ጦር መሳሪያ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል እና የመረጃና ደኅንነት አካላት ባደረጉት የጋራ ዘመቻ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለፀ፡፡

በሶማሌ ክልል አፍዴር ዞን ከሶማሊያ ድንበር አከባቢዎች የተሰማሩ የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ሰራዊትና የመረጃ አካላት አሸባሪው አል-ሸባብ በድንበር ላይ ያከማቹት በርካታ ጦር መሳሪያዎች በባረይ ወረዳ በደዊ ቀበሌ ከ8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር አውለዋል።

በሶማሌ ክልል ልዩ ኹለተኛ ሪጅመንትና የመረጃና ደኅንነት አካላት ባደረጉት የጋራ ዘመቻ 50 AK 47 ወይም ክላሽ ኮቭ፣ 10 RPG መሳሪያዎችና ከ50 ሽጉጦችና በርካታ ጥይቶችን ያካተተ ህገ ወጥ መሳሪያ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገልጿል።

ከዚህ በተጨማሪም የልዩ ኃይል አመራሩ አሸባሪው አል-ሸባብ በኹለቱ አገራት ድንበር ላይ የደበቁት ጦር መሳሪያዎች የሽብር ጥቃቶች ለመፈጸም የተዘጋጁ እንደነበር ገልፀው ዒላማ ያደረጉት አከባቢዎች ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ማረጋገጣቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
_____________________
ትክክለኛውን የአዲስ ማለዳ ሶሻል ሚዲያ በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑ
Telegram ➲ t.ly/SOXU
Facebook ➲ t.ly/flx8
YouTube ➲ t.ly/vSgS
Twitter ➲ t.ly/mxA4n

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here