24 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመመሪያ ጥሰት በመፈጸማቸው ተዘጉ

0
3032

ከባድ የመመሪያ ጥሰት በፈጸሙ 24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃዎች መውሰዱን የትምህርትና ሥልጣና ባለሥልጣን አስታወቀ።
ባለሥልጣኑ ፈቃዳቸውን ከሰረዘባቸው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተጨማሪ ቀላል የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው ለተገኙ 82 ተቋማት የማስጠንቀቂያ ትዕዛዝ መስጠቱን ገልጿል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ በ108 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ147 ካምፓሶቻቸው ላይ ሚያዚያ 10 እና 11 ቀን 2014 በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ ከባድ የመመሪያ ጥሰት ፈጽመው በተገኙ በ24 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ካምፓሶች ላይ የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃዎች መውሰዱን ባለሥልጣኑ ይፋ አድርጓል።
በተጨማሪም በ82 የግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ቀላል የማስጠንቀቂያ እርምጃ የተወሰደ ሲሆን በቀጣይ የተገኘባቸውን ክፍተቶች በማስተካከል ውሳኔው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ለባለሥልጣኑ ሪፖርት እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ተሰጥቷቸዋል።
የፕሮግራም፣ የካምፓስ እና የተቋም መዝጋት እርምጃ የተወሰደባቸውን 24 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሪፍት ቫሊ ዩኒቨርስቲ፣ ዌስተርን ኮሌጅ፣ ኢትዮ ራይዝ ኮሌጅ፣ ፋም ኮሌጅ፣ ኢትዮጲስ ኮሌጅ፣ ይገኙበታል።


ቅጽ 4 ቁጥር 184 ግንቦት 6 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here