10 በ2020 ኢትዮጵያ ከአሜሪካ እርዳታ ያገኘችባቸው ዘርፎች

0
1275

ምንጭ፡- ፎሪን አሲስታንስ (2020)

እንደ ኢትዮጵያ ያሉ አዳጊ ተርታ የተጻፉ ደሃ አገራት፣ እርዳታ እና ብድር ቀላል የማይባል ወጪአቸውን ይሸፍንላቸዋል። በተለይም እርዳታን ስንመለከት፣ በልጽገዋል ከሚባ አገራት ቀላል የማይባሉ እርዳታዎች ባህር አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ።
ከአደጉ አገራት ወደ ደሃ አገራት ሚላከው የእርዳታ መጠን በ2020 ከፍተኛው ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን፣ ይህም 161 ቢሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር። ኢትዮጵያም በዚሁ ዓመት 1ቢሊዮን 213 ሚሊዮን 189 ሺሕ 277 የአሜሪካን ዶላር እርዳታን በተመሳሳይ ዓመት ተቀብላለች። ከፍተኛ እርዳታ ሰጪ ሆኖ በቀዳሚነት የሚገኘው ደግሞ የአሜሪካው ዓለማቀፍ ልማት ኤጀንሲ (USAID) ነው።

እነዚህ እርዳታዎች የምግብ ዋስትናን፣ መሠረታዊ የጤና አገልግሎትን፣ የእናቶችና የሕጻናት ጤና ክብካቤን፣ የቤተሰብ እቅድን፣ የኤችአይቪ መከላከልን፣ የሲቪክ ማኅበረሰብን፣ በግጭት ቦታ ሰላምና መረጋጋትን ለማገዝ የተደረጉ ናቸው።
በዚህ የ2020 የድጋፍ ሰንጠረዥ መሠረት፣ ኢትዮጵያ ከፍተኛ እርዳታን በማግኘት በአፍሪካ ቀዳሚ ስትሆን፣ በዓለም ደግሞ አፍጋኒስታንን (አራት ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ተቀብላለች) ተከትላ በኹለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።


ቅጽ 4 ቁጥር 185 ግንቦት 13 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here