መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናማዕከላዊ ዕዝ አገርን ሊያሸብር የሚያስብ ማናቸውንም የጠላት ኃይል መደምሰስ የሚያስችል ወታደራዊ አቅም...

ማዕከላዊ ዕዝ አገርን ሊያሸብር የሚያስብ ማናቸውንም የጠላት ኃይል መደምሰስ የሚያስችል ወታደራዊ አቅም መገንባቱ ተገለፀ

ዕረቡ ግንቦት 17 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ማዕከላዊ ዕዝ አገርን ሊያሸብር የሚያስብ ማናቸውንም የጠላት ኃይል መደምሰስ የሚያስችል ወታደራዊ አቅም መገንባቱን የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አስታወቀ።

ዕዙ በተለያየ የመሬት ገፅታ ላይ ሊያጋጥም የሚችል ጠላት ላይ ድል ለመቀዳጀት እና ለመደምሰስ የሚያስችለውንም ወታደራዊ ልምምድ ማድረጉ ተገልጿል።

የማዕከላዊ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ዘውዱ በላይ እንዳሉት፤ በተለያየ መንገድ አገር የማፍረስ አጀንዳ ይዘው በመንቀሳቀስ የህዝቡን ሰላም ለማወክ በሚዳክሩ የጥፋት ሃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ እና የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሰራዊታችን ወታደራዊ አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ገንብቷል።

በዕዙ የኮር አዛዥ የሆኑት ብ/ጀኔራል ተስፋዬ ረጋሳ በበኩላቸው፤ “ሠራዊቱ ከዚህ ቀደም ከጠላት ጋር ባካሄዳቸው የአውደ ውጊያ ውሎዎች በርካታ ልምድና ተሞክሮችን እንዳገኘበት ገልፀው፣ አሁን ላይ የተፈጠረለትን ፋታ እደመልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ ያደርጋቸው ወታደራዊ ልምምዶች የዝግጁነት ደረጃውን አሳድጎበታል“ ብለዋል።

በዕዝ ደረጃ በተካሄደው ወታደራዊ ልምምድ ላይ የተገኙ የዕዝ፣ የኮር እና የክፍለ ጦር ከፍተኛ አመራሮች ሰራዊቱ የደረሰበትን ግዳጅ የመፈፀም አቅም ማድነቃቸውንም ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ማዕከላዊ ዕዝ ለኢትዮጵያ ሰላም መጠበቅ እስከ ህይወት ዋጋ መክፈል የሚችሉ የቁርጥ ቀን ልጆች ያሉበት፣ ህብረት ያደመቀው የሠራዊት ክፍል መሆኑ ይታወቃል።

 

ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች