ሐሙስ ግንቦት 18 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የደቡብ ፖሊስ ኮሌጅ ለ10ኛ ጊዜ በማዕረግ ሽግግር ያሰለጠናቸዉ መካከለኛና ከፍተኛ አመራር መኮንኖች በዛሬዉ ዕለት አስመረቀ።
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለማየሁ ማሞ፤ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተስፋዪ ቱንጋሞና የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ተወካይ ምክትል ኮሚሽነር ፋሩቅ በድሩ በጋራ በመሆን በትምህርታቸዉ ብልጫ ላመጡ ሰልጣኝ መኮንኖች የምስክር ወረቀትና ሽልማት ከሰጡ በኋላ የማዕረግ ምልክትም አልብሰዋል።
በምክትል ኮማሽነር ማዕረግ የደቡብ ፖሊስ ኮሌጅ ዳይሬክተር ኮማንደር አብራሀም ቲርካሶ የደበብ ፖሊስ ኮሌጅ የተቋማትን የሰዉ ኃይል ለማሟላኮሌጁ በማዕረግ ሽግግር ለ10ኛ እና ለ7ኛ ጊዜ ያሰለጠናቸዉ ስምንት መቶ ሰማንያ ስምንት ሰልጣኞች ለምረቃ በቅተዋል ሲሉ ገልፀዋል።
ከእነዚህም ውስጥ አምስት መቶ ዘጠና አራቱ ከኢንስፔክተር ወደ ዋና ኢንስፔክተር ዘጠና ሶስቱ ከዋና ሳጅን ወደ ረዳት ኢንስፔክተርነት የማእረግ ሽግግር የሚያደርጉ መሆናቸዉ የገለፁት ዳይሬክተሩ ስልጠናቸዉን አጠናቀዉ ለምረቃ መብቃታቸዉ ተናግረዋል።
ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሆነ፤ ሰልጣኞች ከደቡብ፤ ከሲዳማና ከደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ሦስቱ ክልሎች የተወጣጡና በሥራ ላይ የቆዩ የፓሊስ አመራርና አባላት ሲሆኑ፤ 611 ወንድ 75ቱ ሴቶች መሆናቸዉም ለማወቅ ተችሏል።







