መነሻ ገጽማረፊያ10ቱ10 ባለሀብት የሆኑ አፍሪካውያን መሪዎች

10 ባለሀብት የሆኑ አፍሪካውያን መሪዎች

ምንጭ፡-አፍሪካን ኤክስፖነንት (2022)

አፍሪካ እንዳላት የተፈጥሮ ጸጋ ሳይሆንላት የቀረ፣ ድሃ የምትባልና ብዙ ሕዝቧ በችግርና በጦርነት ውስጥ የሚማቅቅ አኅጉር ናት። ይሁን እንጂ ባለሀብት የሚባሉ መሪዎች አሏት። በዚህ ዝርዝር መሠረት የሞሮኮው ንጉሥ ቀዳሚ ሲሆኑ፣ ያላቸው የሀብት መጠን 5.7 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ይጠጋል።
ይህንንም ያፈሩት በተሰማሩበት የኢንቨስትመንት ዘርፍ እንደሆነና በአገራቸው ሪል ስቴትን ጨምሮ፣ በቱሪዝም፣ በቴሌ፣ በሲሚንቶ ፋብሪካ እና በባንክ መስኮች ላይ ተሳትፎ እንዳላቸው ዘ አፍሪካን ኤክስፖነንት በገጹ አስነብቧል።

ከእርሳቸው በመቀጠል በሰፊ ልዩነት ኹለተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት የጋቦኑ ኦንዲምባ ሲሆኑ፣ የእርሳቸው የሀብት መጠን አንድ ቢሊዮን ዶላር ይጠጋል። የተቀሩት በመቶ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ሀብት ያላቸው ሲሆን፣ ይህም ከ500 እስከ 200 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል። በ10ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት የግብጹ አል ሲሲ የሀብት መጠን 185 ሚሊዮን ዶላር ይገመታል።

እነዚህ መሪዎች ምንም እንኳ በየአገራቸው የተለያየ መስክ ላይ የተሰማሩ ቢሆኑም፣ ሙስና እንግዳ ባልሆነባት አፍሪካ የሀብታቸው ምንጭ ጤናማ ነው ለማለት ብዙዎች ይቸገራሉ። ሆኖም ግን በመልካም ምግባር ሆነው በልፋታቸው ሀብት ያፈሩም እንዳሉ እሙን ነው።


ቅጽ 4 ቁጥር 186 ግንቦት 20 2014

ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች