መነሻ ገጽዜናአቦል ዜናድንበር አቋርጠው ከገቡ ተሽከርካሪዎችና ከታሪፎች 2.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኘ

ድንበር አቋርጠው ከገቡ ተሽከርካሪዎችና ከታሪፎች 2.3 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኘ

ከባለፈው ዓመት አንጻር ገቢው በ1 ቢሊዮን ብር አድጓል

ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ድንበር አቋርጠው ከውጭ አገራት ከገቡ ተሽከርካሪዎች እና ከተጨማሪ ዘርፎች መገኘቱን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

በበጀት ዓመቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት በነዳጅ ላይ ከተጣለ ታሪፍ፣ ከተሽከርካሪ ቅባትና ዘይት እንዲሁም በመንገድ ጠቀሜታ ላይ ከተጣለ ታሪፍ እና በክብደት ላይ ከተመሠረተ የተሽከርካሪ ፈቃድ ማደሻ፣ በአጠቃላይ ከአራት የገቢ ምንጮች ከ2 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አስራት አሰሌ ለአዲስ ማለዳ አስታውቀዋል።

የነዳጅ አቅርቦት ከሌሎች አገራት ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ ለተለያዩ የነዳጅ ማደያዎች ከመከፋፈሉ በፊት ከተጣለ ታሪፍ ከ200 ሚሊዮን 185 ሺሕ ብር በላይ፣ ከውጭ አገራት የገቡ ተሽከርካሪዎች የሚጠቀሙባቸው ቅባትና ዘይት ላይ ከተጣለ ታሪፍ ከ3 ሚሊዮን 185 ሺሕ ብር በላይ ገቢ መገቱን ኃላፊው ጠቁመዋል።
ኃላፊው አክለውም ከጅቡቲ፣ ከኬንያ እና ከሌሎች አገራት በሕጋዊ መንገድ ድንበር አቋርጠው ከገቡ ተሽከርካሪዎች ወይም ከመንገድ ጠቀሜታ ታሪፍ 3 ሚሊዮን 578 ሺሕ 97 ብር፣ ከሕዝብ ተሽከርካሪዎች እስከ ከባድ ተሽከርካሪ ከተሰበሰበ ዓመታዊ የተሽከርካሪዎች ማደሻ ክፍያ 175 ሚሊዮን 790 ሺሕ 870 ብር በድምሩ ከ2 ሚሊዮን 368 ሺሕ ብር ያላነሰ ገቢ ተገኝቷል ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለማግኘት ከተቀመጠው እቅድ አንፃር 90 ነጥብ 96 በመቶ መሰብሰብ የተቻለ ቢሆንም፣ የኮቪዲ 19 ወረርሽኝ እና በኢትዮጵያ ያላው የፀጥታ ችግር ለተያዘው እቅድ አለመሳካት ተጠቃሽ ምክንያት መሆናቸው ተጠቅሷል።
ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር፣ ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ ብልጫ እንዳለው እና ለዚህም ተቋሙ ከአጋር ተቋማት ጋር በቅንጅት የተጠናከረ ሥራ መሥራት መቻሉ ለገቢው አስተዋፅኦ አበርክቷል ተብሏል።

የተሰበሰበው ገቢ ለመንገድ ጥገና ለማዋል ታስቦ ለኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን 1 ነጥብ 97 ሚሊዮን 812 ሺሕ 357 ብር፣ ለክልል መንገድ ኤጀንሲዎች 3 ነጥብ 715 ሺሕ 802 ብር፣ ለከተማ መንገድ ኤጀንሲዎች ከ1 ሚሊዮን 829 ሺሕ ብር በላይ ገቢ መደረጉ ተነግሯል።

ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ በማሰባሰብ ለፌዴራል፣ ለክልል እና ለተለያዩ ከተማ መንገድ ኤጀንሲዎች በመመደብ ከአምስት መቶ ሺሕ ኪሎ ሜትር በላይ መንገዶች የጥገና ሥራ እንዲከናወን ማድረግ እንደተቻለ እና ለመንገድ ዘርፉ እስከ 15 በመቶ የጥገና ወጪን መሸፈን ችሏል ተብሏል።
መንገዶች ምቹ አገልግሎትን በዘላቂነት እንዲሰጡ በየጊዜው ወቅታዊና መደበኛ ጥገና እንዲሁም ድንገተኛ ጥገናዎች የሚያስፈልጋቸው ሲሆን፣ መንገዶች ተገቢውን ጥገና በወቅቱ እንዲያገኙ እና ለመንገድና ትራፊክ ደኅንነት ሥራዎች ትኩረት ተሰጥቷል ተብሏል።

የመንገድ ፈንድ ገቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ሲሆን፣ በመጀመሪያዎቹ ዓመታት 300 ሚሊዮን አካባቢ የነበረ ሲሆን፣ በተያዘው ዓመት ከፍተኛ ጭማሬ ማሳየቱ ተጠቁሟል።


ቅጽ 4 ቁጥር 186 ግንቦት 20 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች