መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናወደ ትግራይ ክልል ከሃምሌ ወር ጀምሮ እስካሁን ድርስ ከ1 ነጥብ 87 ቢሊዮን...

ወደ ትግራይ ክልል ከሃምሌ ወር ጀምሮ እስካሁን ድርስ ከ1 ነጥብ 87 ቢሊዮን በላይ ብር መላኩ ተገለጸ

ሰኞ ግንቦት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ወደ ትግራይ ክልል ከሃምሌ ወር ጀምሮ እስካሁን ድርስ ከ1 ነጥብ 87 ቢሊዮን በላይ ብር መላኩን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።

የኮሚሽኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ደበበ ዘውዴ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እንደተናገሩት፤ ሰሜን ኢትዮጵያ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት መሰረታዊ የሚባሉ ድጋፎች በተለያየ መልኩ ወደ ትግራይ ክልል እየተላከ ይገኛል።

በዚህም ከሃምሌ ወር ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በ93 አጋር ድርጅቶች በኩል ከ1 ነጥብ 87 ቢሊዮን ብር በላይ የጥሬ ገንዘብ ዝውውር መደረጉን ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም በእነዚሁ የተለያዩ አጋር አካላት አማካኝነት 202ˏ79 መድኃኒት፣ 102 ሺህ 226 ኪሎ ግራም ምግብ ነክ ያልሆኑ እርዳታ እና 409 ሺህ 322 ኩንታል የተመጣጠነ ምግብ በአየር ትራንስፖርት መላኩን ገልጸዋል፡፡

በየብስ ትራንስፖርት ደግሞ በርካታ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን፤ ለአብነትም 402ˏ229 ሊትር ነዳጅ ጨምሮ እስካሁን ወደ ትግራይ ክልል የተሰማራዉ የጭነት ተሽከርካሪ ብዛት 1ሺህ 947 ደርሷል፡፡ በአጠቃላይ ለሰብአዊ አገልግሎት የተከናወነው በረራ 223 መሆኑን ደበበ ጨምረው ለሬዲዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች