ኢሰመጉ የ2022 የሰብአዊ መብቶች ሽልማትን ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሊቀበል ነው

0
1229

ሰኞ ግንቦት 22 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) የ2022 የሰብአዊ መብቶች ሽልማት ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል የጀርመን ክፍል በዛሬው ዕለት ሊቀበል መሆኑን አስታወቀ።

ሽልማቱ ኢሰመጉ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በመሆኑ እንዲሁም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ህይወት ስጋት ውስጥ በሚከቱ ከባድ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን መስራት በመቻሉ የሚሰጠው እውቅና መሆኑ ተገልጿል።

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዳን ይርጋ ከጀርመን ሆነው ከጠዋቱ 5 ሰዓት ከ50 ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡ ሲሆን፣ ይህም መግለጫ በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች በቀጥታ ተላልፏል።

ዋናው ሽልማት ከምሽት 3:00 ጀምሮ የሚከናወን ሲሆን፤ https://www.youtube.com/c/AmnestyDeutschland ሊንክን በመጠቀም በቀጥታ መከታተል እንደሚቻል ኢሰመጉ አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here