ምስራቃዊ የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ በኢትዮጰያ በኩል ተጠናቀቀ

0
486

ከኢትዮጵያ ኢንያ ድረስ የሚዘረጋው እና በኢትዮጵያ በኩል  437 ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍነው መስራቃዊ የኤሌክትሪክ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ በኩል ያለው ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ ተገለፀ። በቻይናው ኩባንያ ቻይና ኤሌክትሪክ ፓወር ቴክኖሎጂ የሚገነባው ፕሮጀክቱ ከወላይ ታ ሶዶ በመነሳት ኬንያ ድረስ የሚዘልቀው የኤሌክትሪክ መስመር 500 ኪሎ ቮልት የሚሸከም ሲሆን የኹለቱን አገራት የኃይል ማሰራጫዎችን የሚያገናኝ ይሆናል።

በቀጣይ ደግሞ በኬንያ በኩል ያለው ፕጀክት የሚጠበቅ ሲሆን ይህም 622 ኪሊ ሚቴሮችን እንደሚረዝም ለማወቅ ተችሏል። በኬንያ በኩል ያለው መስመር ዝርጋታ በጀርመኑ ሲመንስ ኩባንያ እንደሚከናወንም ታውቋል። ለፕሮጀክቱ 1 ነጥብ 2 በሊዮን ዶላር ወጪ የሚደረግ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 88 ሚሊዮን ዶላር በኬንያ መንግስት የሚሸፈን ሲሆን 32 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከኢትዮጵያ መንግስት ወጪ ይደረጋል። ቀሪው ደግሞ 684 ሚሊዮን ከአለም ባንክ በተገኘ ብድር፣ 338 ሚሊዮን ዶላር ከአፍሪካ ልማት ባንክ እዲሁም 118 ሚሊዮን ዶላር ደግሞ ከፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ በሚገኝ ብድር ተግባራዊ ይሆናል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here