10ቱ በአፍሪካ ከፍተኛ ኢንተርኔት ተጠቃሚ ያሉባቸው አገራት

0
738

የኢንተርኔትና ማኅበራዊ ሚድያ አጠቃቀም በተለያየ ጊዜ በአዎንታዊና በአሉታዊ ጎኑ ይነሳል። ትልልቅ ለውጦችን ከማምጣትና በጎ ተጽዕኖ ከማምጣ ጀምሮ፤ ወደለየለት ብጥብጥና ኹከት የሚነዱ የሐሰት መረጃዎች በኢንተርኔት አማካኝነት በማኅበራዊ ድረ ገጽ እንደሚሰራጩና እንደሚጋሩ ይታወቃል። ጎን ለጎንም የኢንተርኔት ተጠቃሚ ቁጥር በየጊዜው እየጨመረ ይገኛል። ኢንተርኔት ወርልድ ስታተስ የተባለ ድረገጽ ከወራት በፊት ባወጣው መረጃ መሠረት ደግሞ፤ በአፍሪካ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ2000 (እ.ኤ.አ.) ጀምሮ 116 አጥፍ አድጓል።

በአፍሪካ በአሁን ሰዓት 525 ሚሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እንዳሉ መረጃ ይጠቁማል። በአንጻሩ 447 ሚሊዮን ተጠቃሚዎች በላቲን አሜሪካና ካረቢያን፣ 328 ሚሊዮን በደቡብ አሜሪካ እንዲሁም 174 የኢንተርነት ተጠቃሚዎች በመካከለኛው ምሥራቅ ይገኛሉ። አፍሪካ ከእነዚህ አሕጉራትና ክፍለ አሕጉራት ሁሉ የበለጠ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ሕዝብ አላት ማለት ነው።

ከዚህ ውስጥ ደግሞ ናይጄሪያ ከአፍሪካ የኢንተርኔት ተጠቃሚ ከሆኑ አገራት በሕዝብ ድርሻ 20 በመቶ በመያዝ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ከናይጄሪያ ቀጥሎ ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላት ኢትዮጵያ ደግሞ በ20.5 ሚሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች በስምንተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ቅጽ 1 ቁጥር 47 መስከረም 17 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here