የዓለም ባንክ ግሩፕ ለኢትዮጵያ የ200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሊያደርግ ነው

0
730

ዕረቡ ግንቦት 24 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የዓለም ባንክ ግሩፕ ኢትዮጵያ ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር የነደፈቻቸውን ስትራቴጂካዊ ሀሳቦች ለማገዝ የ200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ።

ከዓለም ባንክ ግሩፕ ዋሽንግተን ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የመንግሥት ቴክኒክ እና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትን አቅም በመገንባት፤ የሥራ ገበያው የሚፈልገውን በክህሎት የዳበረ የሰው ኃይል በማፍራት ጥራት ያለው የሥራ ዕድል ለመፍጠር የተነደፈው ስትራቴጂካዊ ሐሳቦች ላይ ውይይት ማድረጋቸውን የሥራ እና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል በማኅበራዊ ትሥሥር ገጸቸው ባሰፈሩት መልእክት ገልጸዋል።

በዚህም “ባንኩ 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ ተስማምተናል” ብለዋል።

ሚኒስትሯ የዓለም ባንክ በተለያዩ ዘርፎች እያደረገ ላለው እገዛ በተለይም የፕሮግራሙን ሐሳብ አዋጭነት ገምግመው ለተግባራዊነቱ እገዛ ላደረጉት ሳፋ ኤሊ ኮጋሊ፣ ሁማ አሊ ዋሂድ እና ባልደረቦቻቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here