በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሸከርካሪዎች የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ ነው

0
1065

ሰኞ ግንቦት 29 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በመዲናዋ አዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስ እና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ይፋ ሊደረግ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በመዲናዋ ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የሚዲ-ባስና ሚኒ-ባስ ተሽከርካሪዎች አዲስ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ነገ ዕለተ ማክሰኞ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ለሚዲያ ተቋማት ይፋ ይደረጋል ተብሏል፡፡

የታሪፍ ማሻሻያው ከሰኔ 01 ቀን 2014 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ አፈፃፀሙ በተገቢው እንዲከወን የህግ አስከባሪ አካላት ሚና የጎላ ነው ያለው ቢሮው፤ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ አሳስቧል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞ ህብረተሰቡ የሚወጣውን ትክክለኛ ታሪፍ አውቆ በመክፈልና ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማጋለጥ በኩል ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን ድርሻ በመወጣት እንዲተባበር ቢሮው መልዕክቱን አስተላልፋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here