በአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ ላይ የዋጋ ማስተካከያ እንደሚደረግ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ

0
1215

የፌዴራሉ መንግሥት ለአፈር ማዳበሪያ ግዥ 15 ቢሊዮን ብር ድጎማ ማድረጉን ተከትሎ በአፈር ማዳበሪያ ሽያጭ ላይ የዋጋ ማስተካከያ እንደሚደረግ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ።

ክልሉ ለ2014/15 ምርት ዘመን ካቀደው የአፈር ማዳበሪያ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ኩንታል ወደ ክልሉ ገብቶ እየተሰራጨ እንደሚገኝ ነው ቢሮው የገለጸው።

ወደ ኀብረት ሥራ ማኅበራት ከ3 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ የተጓጓዘ ሲሆን፣ እስከ አሁን 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሩ መሠራጨቱን አመላክቷል።

የድጎማ አፈፃፀሙን በተመለከተ ግብርና ሚኒስቴር በሚያወርደው አሠራርና አቅጣጫ መሠረት የሚፈፀም ይሆናልም ነው የተባለው።
አቅርቦትና ስርጭቱን ፍትሐዊ ለማድረግ፣ ለታለመለት ዓላማ እንዲውልና ሕገ ወጥነትን ለመከላከል ቢሮው ክትትልና ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቅሶ፣ አልፎ አልፎ የሚታዩ ችግሮች ሲኖሩ በወቅቱ እንዲስተካከል እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።

ምርጥ ዘር በተለይ የበቆሎ ሰብል ቀድሞ የሚዘራ በመሆኑ፣ ከቀረበው 93 ሺሕ 869 ኩንታል ውስጥ እስከ አሁን 76 ሺሕ 667 ኩንታል ተሰራጭቷል ተብሏል።

የአፈር አሲዳማነትን በማከም ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው ‹‹ኖራ›› ትኩረት ተሰጥቶት እየተሠራ ሲሆን፣ ከቀረበው 39 ሺሕ 327 ኩንታል ኖራ ውስጥ 21 ሺሕ 495 ኩንታል መሰራጨቱም እንዲሁ ተጠቁሟል።


ቅጽ 4 ቁጥር 189 ሰኔ 11 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here