መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናበአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እየተሰጠ ነው

ሰኞ ሰኔ 27 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና በኹሉም ክፍለ ከተሞች እየተሰጠ ይገኛል።

በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ያለምንም ችግር እየወሰዱ ሲሆን፤ ፈተናው ለ3 ተከታታይ ቀናት እንደሚቆይ ተገልጿል።

የፈተና ደኅንነት ለመጠበቅ እና የፈተናውን ሂደት ለመከታተልም ቀደም ሲል የተዋቀረው ኮማንድ ፖስት 10 የፀጥታ አካላት ማሰማራቱ ተገልጿል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ 179 የመፈተኛ ጣቢያዎች የሚገኙ ሲሆን፤ በዚህም 71 ሺሕ 832 የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ ከከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች