ማክሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ)በአማራ ክልል የ2014 የ8ኛ ክፍል ፈተና ዛሬ መሰጠት ጀምሯል።
ፈተናውን ከ359 ሺህ በላይ ተማሪዎች፤ በክልሉ በሚገኙ 5 ሺህ 395 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚወስዱ ሲሆን፤ ከ10 ሺህ በላይ መምህራን ፈተናውን በመስጠት እንደሚሳተፋም የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።
ከተፈታኞች መካከል ከ1 መቶ 93 ሺህ በላይ ወይንም 53 ነጥብ 8 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች መሆናቸውም ተገልጿል፡፡
ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ድረስ ለሦስት ቀናት ይሰጣልም ተብሏል።




