መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናኢትዮጵያ እና ሱዳን በመካከላቸው ያሉ ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት...

ኢትዮጵያ እና ሱዳን በመካከላቸው ያሉ ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸው ገለፁ

ማክሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ እና ሱዳን በመካከላቸው ያሉ ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኝነታችንን ገልጸናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።

በ39ኛው የኢጋድ መሪዎች አስቸኳይ ጉባኤ ለመሳተፍ ኬንያ፤ ናይሮቢ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል-ቡርሃን ጋር ውይይት አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት “ኹለቱ አገራት በሰላማዊ መንገድ ሊሠሩባቸው የሚችሉ በርካታ የትብብር መሠረቶች እንዳሏቸው አረጋግጠናል ” ብለዋል።

“ያለን ትሥሥር ከየትኛውም መከፋፈል የሚበልጥ ነው ” ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ” ኹለታችንም ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮችን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኝነታችንን ገልጸናል” ሲሉ አሳውቀዋል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች