የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ጭማሪ መደረጉ ተገለፀ

0
2688

ማክሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ከነገ ሰኔ 29 ቀን 2014 እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2014 የነዳጅ ምርቶች የመሸጫ ዋጋ ጭማሬ መደረጉን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ታህሳስ 20 ቀን 2014 ባደረገው 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ባስተላለፈው የነዳጅ ውጤቶች የዋጋ ግንባታና የትርፍ ህዳግ አሰራር እና የመሸጫ ዋጋ ማስተካከያና የታለመ ድጎማ አፈጻጸም ውሳኔ ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ሥራ ሲከናወን መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ሚኒስቴሩ በላከው መግለጫ መሰረት÷

* ቤንዚን—-47 ነጥብ 83 በሊትር

* ነጭ ናፍጣ ….49 ነጥብ 02 በሊትር

*ኬሮሲን…49 ነጥብ 02 በሊትር

* ቀላል ጥቁር ናፍጣ…53 ነጥብ 10 በሊትር

* ከባድ ጥቁር ናፍጣ…52 ነጥብ 37 በሊትር

* የአውሮፕላን ነዳጅ…98 ነጥብ 83 በሊትር መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከላይ የተገለጸው የቤንዚን፣ የኬሮሲንና የነጭ ዋጋ ላይ ለህዝብ ትራንስፖርት ተሽከርካሪዎች ወይም የታለመ ድጎማ ተጠቃሚ ተሸከርካሪዎች 15 በመቶ በመንግስት እንዲደጎሙና ቀሪውን 10 በመቶ እንዲከፍሉ በማድረግ የድጎማ መጠኑን በቴሌ ብር ተመላሽ እንዲሆንላቸው እንደሚደረግም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

የተደረገው የዋጋ ማስተካከያ የተደረገባቸው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዝርዝር ከነገው /ሰኔ 29 ቀን 2014 ጀምሮ በኹሉም ክልሎች በሚገኙ ማደያዎች ኹሉ ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here