የአደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት ምትኩ ካሳ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

0
1257

ዕረቡ ሐምሌ 6 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ምትኩ ካሳ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ነው በዛሬው ዕለት በፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተገለጸ።

በፌዴራል ፖሊስ በወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ መምሪያ ሀላፊ ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ አያሌው ለኢቢሲ እንዳሉት፣ ኮሚሽነሩ በቁጥጥር ሥር የዋሉት “ኤልሻዳይ” ከተሰኘ በጎ አድራጎት ማህበር ባለቤት ጋር በመመሳጠር የሙስና ወንጀል ፈፅመዋል በሚል በመጠርጠራቸው ነው።

ይህ ኤልሻዳይ የተሰኘ ድርጅት በአዋሽ፣ በአዳማ፣ በሀዋሳ፣ በእንጅባራ እና በሌሎችም አካባቢዎች ተፈናቃዮች በሌሉበት ተፈናቃዮች አሉ በማለት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርዳታ እህልና አልባሳት በመረከብ ሽጦ ለተጠርጣሪው መኖሪያ ቤት መግዛቱ በምርምራ መረጋገጡን ነው ረዳት ኮሚሽነር ታደሰ የተናገሩት።

ፖሊስ በተጠርጣሪው ላይ ሰፊ ክትትል ሲያደርግ እንደነበረም ረዳት ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here