መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናዶ/ር መሉቀን ሀፍቱ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ዋሉ

ዶ/ር መሉቀን ሀፍቱ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ዋሉ

አርብ ሐምሌ 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ሃላፊ የነበሩትና ያለመከሰስ መብታቸው በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የተነሳው ሙሉቀን ሀፍቱ (ዶ/ር) ከአዲስ አበባ ምክር ቤት ስብሰባ እንደወጡ ሲቪል በለበሱ ሰዎች ተይዘዋል።

ሙሉቀን ከቅርብ ደቂቃዎች በፊት ከአዲስ አበባ ምክር ቤት ስብሰባ በመውጣት ላይ ሳሉ በመንግሥት የጸጥታ ኃይል ተይዘው መወሰዳቸውን በቦታው የነበረው የአዲስ ማለዳ ዘጋቢ ተመልክቷል።

የፍትህ ሚኒስቴር ከጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ ማውጣት ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አባልና የአዲስ አበባ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊውን ሙሉቀን ሀፍቱ (ዶ/ር) ያለመከሰስ መብታቸው ዛሬ ጠዋት መነሳቱ የሚታወስ ነው።

ያለመከሰስ መብት ይነሳልን ጥያቄው፤ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች እጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ እና የተሰጣቸውን ስልጣንና ኃላፊነት በአግባቡ ባለመጠቀም በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለው እንዲጣራ ለማድረግ መሆኑ በምክር ቤቱ ተነስቶል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች