መነሻ ገጽማረፊያ10ቱ10 በዓለማችን ከፍተኛ ቡና አምራች አገራት

10 በዓለማችን ከፍተኛ ቡና አምራች አገራት

ምንጭ፡-ቪዥዋል ካፒታሊስት (2021)

ቡና በዓለማችን ተወዳጅ ከሆኑ መጠጦች መካከል ከቀዳሚዎቹ ይገኛል። በዓለምም ከውሃ እና ሻይ ቀጥሎ በሦስተኛ ደረጃ ብዙ የሚወሰድ መጠጥ ሆኖ ተቀምጧል።

ከሰባ በላይ አገራት ቡናን ሲያመርቱ፣ እነዚህ ዐስርቱ ደግሞ በዓመት በቢሊዮን የሚቆጠር ኪሎግራም ቡናን ወደ ገበያ ያቀርባሉ። እነዚህም ከዓለም ገበያ ላይ የየራሳቸው ድርሻን ይዘው ምርታቸውን ለገበያ ለተጠቃሚ ያደርሳሉ። በ2020 በነበረው ምርትም እነዚህ ዐስርቱ ከፍተኛ ቡና አምራች አገራት በዓለም ገበያ 87 በመቶውን ድርሻ ጠቅልለው ይዘው ነበር። ኢትዮጵያም በዚህ ዝርዝር በአምስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ከብራዚል እና ከቬትናም አንጻር በገበያ ውስጥ የኢትዮጵያ ቡና ያለው ድርሻ አነስተኛ የሚባል ቢሆንም፤ ቡናዋ ተፈላጊ በመሆኑ ትንሽ የሚባል ጥረትም ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችል እንደሆነ ይታመናል።


ቅጽ 4 ቁጥር 195 ሐምሌ 23 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች