መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናበኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የንግድ ቀጠና በድሬዳዋ በይፋ ሥራ ለማስጀመር የመጨረሻው ምዕራፍ ዝግጅት እየተጠናቀቀ...

በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የንግድ ቀጠና በድሬዳዋ በይፋ ሥራ ለማስጀመር የመጨረሻው ምዕራፍ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑ ተገለፀ

አርብ ሐምሌ 29 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የንግድ ቀጠና በድሬዳዋ በይፋ ሥራ ለማስጀመር የመጨረሻው ምዕራፍ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የስትራቴጂ አማካሪ ኪያ ተካልኝ አስታወቁ።

አማካሪው ይህንን የገለፁት የተለያዩ የአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሀን ድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክን በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡

በጉብኝቱ ላይም አማካሪው በሰጡት ገለፃ፤ ነፃ የንግድ ቀጠናውን ምስረታ ለማስጀመር አስፈላጊ የመሰረተ ለማት ሥራዎቸ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በኩል መጠናቀቃቸውን አንስተዋል፡፡

ነፃ የንግድ ቀጣናው በሦስት መሰረታዊ ነገሮች ላይ እንደሚያተኩር ያሳወቁት የስትራቴጂ አማካሪው፤ እነርሱም ለአገር ውስጥ እና ለውጪ ገበያ የሚሰሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች፣ አስመጪና ላኪ ድርጅቶች እንዲሁም ቀልጣፋ የሆነ የሎጀስቲክስ አገልግሎት የሚሰጥበት ቀጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ነፃ የንግድ ቀጠናው የሚያተኩርባቸውን ዘርፎች ለማሳለጥ አጋዥ የሆኑ አገልግሎቶችም የሚሰጡ መሆኑንም በማንሳት፤ የባንክ፣ የኢንሹራንስ፣ የማማከር እና ድጋፍ አገልግሎቶች በዋነኝነት የሚጠቀሱት ሲሆኑ ተቀናጅተውም አገልግሎቱን የሚሰጡ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ኪያ በመግለጫቸው በአለማችን ከ5000 በላይ ነፃ የንግድ ቀጠናዎች እንደለሙ አስታውሰው፤ ያደጉት አገራት የእድገታቸው ዋነኛ መሰረት እነዚህ ነፃ የንግድ ቀጣናዎች መሆናቸው በብዙ ጥናቶች ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ነፃ የንግድ ቀጠናውን ሥራ ለማስጀመር በዘርፉ የረጅም ግዜ ልምድ ካላቸው አገራት ሰፊ ልምዶች መቀሰማቸውን አስታውሰዋል፡፡

አክለውም፤ በዋነኝነት የውጪ ንግድን ለማሳለጥና ለማሳደግ፣ ሰፊ የሆነ የሥራ እድል ለመፍጠር፣ ተኪ ምርቶችን ለማሳደግ፣ የእውቀት ሽግግርን ለማሳለጥ እንዲሁም ለአገር ውስጥ የቀረቡ ምርቶችን ለማከማቸትና የሎጀስቲክስ ወጪን ለመቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም አብራርተዋል፡፡

በአገር ውስጥ የሸቀጥ ዋጋዎች ላይ ወጪን የመቀነስና በአገራችን እየተስተዋለ የሚገኘውን የዋጋ ግሽበት ለማረጋጋት፤ እንዲሁም የእሴት ሰንሰለቱን ለማጠናከር አይነተኛ ሚና እንደሚጫወትም በመግለጫቸው አመላተዋል፡፡

በቀጠናው የአገሪቱ የጉምሩክ ሥርዓት ልማቱን ለማሳለጥ በሚያስችል ሁኔታ የሚተገበር ሲሆን በቀጠናው በኢንቨስትመንት የሚሰማሩ ባለሀብቶች፣ ድርጅቶችና አስመጪና ላኪዎች ዘርፈ ብዙ ማበረታቻዎች እንሚቀርቡላቸው በመግለጫው መነገሩን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና የህግ ማዕቀፎች፣ የመሰረተ ልማት ዝግጅቶች እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ የተጠናቀቁ ሲሆን፤ በቅርቡም በይፋ ሥራ እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች