መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናፖሊስ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር በነበሩት ምትኩ ካሳ ልጅ ሥም...

ፖሊስ የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር በነበሩት ምትኩ ካሳ ልጅ ሥም የተገዙ ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችና አንድ መኖሪያ ቤት ማግኘቱን ገለጸ

በተጨማሪም 8 ሚሊዮን 300 ሺሕ ብር ለዕንይ ሪል ስቴት የተከፈለበት ሲፒኦ ማግኘቱንም ለፍርድ ቤት አስረድቷል

ሰኞ ነሐሴ 2 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አድርጎ መጠቀም ሙስና ወንጀል ተጠርጣሮ ከብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር ከነበሩት ከአባቱ ከምትኩ ካሳ ጋር በቁጥጥር ሥር በዋለው እያሱ ምትኩ ሥም የተገዙ ተጨማሪ ተሽከርካሪዎችና አንድ መኖሪያ ቤት ማግኘቱን ፖሊስ አስታወቀ።

እያሱ ምትኩ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡ ተነጥሎ ለብቻው ዛሬ ለ3ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀርቧል።

ተጠርጣሪው ከኤልሻዳይ ድርጅት በወር 15 ሺህ ብር ለቤት ኪራይ ለአምስት ዓመት ከተከፈለለት 900 ሺሕ ብር እና በሥሙ የተገዙ ኹለት ተሽከርካሪዎች ውጪ ተጨማሪ ተሽከርካሪዎች በሥሙ የተገዛበት ማስረጃ መኖሩን ፖሊስ ጠቅሷል።

መርማሪ ፖሊስ በባለፈው ቀጠሮ ተጠርጣሪው ከአባቱ መዝገብ ተነጥሎ በተሰጠው የ10 ቀን የምርመራ ጊዜ ውስጥ የሰራውን የምርመራ ሥራን ተከትሎ ያገኘውን የምርመራ ውጤት ለፍርድ ቤቱ ገልጿል።

በዚህም፤ ተጠርጣሪው በፊት በሥሙ ከተገዙ ኹለት ተሽከርካሪዎች በተጨማሪ ሌላ በሥሙ የተገዙ ኹለት ተሽከርካሪዎች መገኘታቸውን መርመሪ ፖሊስ ገልጿል።

እንዲሁም ተጨማሪ አንድ መኖሪያ ቤት በሥሙ መገዛቱን የገለጸው ፖሊስ፤ ለዕንይ ሪል እስቴት 8 ሚሊዮን 300 ሺሕ ብር የተከፈለ ሲፒኦ ማግኘቱን አያይዞ ለፍርድ ቤቱ አብራርቷል።

መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪው ለቤት እቃ በሚል ከአስመጪዎች ግዢ የተፈጸመበትን ማስረጃ ማግኘቱንም ጨምሮ አስረድቷል።

በተጠርጣሪው ላይ ኹለት ምስክር ቃል መቀበሉን የገለጸው መርማሪ ፖሊስ፤ አሽከርካሪና ተሽከርካሪ ባለስልጣን ማስረጃ ለመሰብሰብ ደብዳቤ መጻፉን ገልጿል።

ለንግድ ባንክ ማስረጃ ለመሰብሰብ እንዲያስችለው ደብዳቤ ጽፎ ውጤቱን እየተጠባበቀ መሆኑን እና ቀሪ የአምስት ምስክሮች ቃል የመቀበል ሥራ እንደሚቀረው አብራርቷል።
ተጨማሪ ማስረጃ ለማሰባሰብ 14 ቀን እንዲሰጠው ጠይቋል።

በፍርድ ቤቱ በኩል ግን ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጡት የምርመራ ጊዜ የአምስት ምስክሮችን ቃል እስካሁን ለምን እንዳልተቀበለ የተጠየቀ ሲሆን፤ ምስከሰሮቹ የተለያየ ቦታ በመሆናቸውና በአድራሻቸው ባለመገኘታቸው ምክንያት መቀበል ሳይችል መቅረቱን ጠቅሶ መልስ ሰጥቷል።

የተጠርጣሪ ጠበቆች ፈቱ ኑሬና እና ሀብተማርያም ፀጋዬ በበኩላቸው፤ ደንበኛችን በተጠረጠረበት በወንጀል የተገኘ ገንዘብን ህጋዊ አድርጎ መጠቀም ሙስና ወንጀል እስከአሁን ለፖሊስ የተሰጠው የ24 ቀን ጊዜ ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት ጋር አለው ወይስ የለውም የሚለውን ጉዳይ ለማጣራት በቂ እንደነበር ገልጸዋል።

ፖሊስ በባለፈው ቀጠሮ ከተሰጠው የምርመራ ጉዳይ ውጪ ሌላ የዕቃ ግዢ ላይ ማስረጃ አግኝቻለው ብሎ ማቅረቡ ከማቋቋሚያው ፍሬ ነገር አንጻር ተገቢ አደለም ሲሉ ጠበቆቹ የመከራከሪያ ነጥብ አንስተዋል።

የማቋቋሚያ ፍሬ ነገርን በተመለከተ ለኛ ይተው የኛ ሥራ ነው ሲሉ መልስ የሰጡት መዝገቡን የተመለከቱት ዳኞች፤ በጊዜ ቀጠሮ በሚሰጠው የምርመራ ጊዜ ፖሊስ ተጨማሪ ማስረጃ መሰብሰብና ማቅረብ እንደሚችል አስገንዝበዋል።

በጠበቆች በኩል የደንበኛችን አባት ታስረው ባሉበትና ባለቤታቸው ለወሊድ በተዘጋጁበት ሂደት እሳቸውን አስሮ ማቆየት የሞራል ጥያቄ ያስከትላል የሚል አስተያየት ተሰጥቷል።

ደንበኛችን ከተቋም የሚሰበሰብ ማስረጃን ሊያደናቅፍ የሚችልበት ሁኔታ የለም ሲሉ የተከራከሩት ጠበቆቹ፤ የአንድ ልጅ አባት መሆኑን ገልጸው ባለቤታቸው ለኹለተኛ ልጅ ለመውለድ በዝግጅት ላይ መሆኗን አብራርተዋል።

- ይከተሉን -Social Media

በዚህ ኹኔታ ላይ ተጠርጣሪውን ታስረው በፖሊስ የተጠየቀው የተጨማሪ ጊዜ ቀጠሮ ሊፈቀድ አይገባም ሲሉ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ጠበቆቹ የተጠረጠረበት ወንጀል ዋስትና እንደማያስከለክል ገልጸው፤ ደንበኛቸው በዋስ ወጥቶ ምርመራው እንዲቀጥል ፍርድ ቤቱን ጠይቀዋል።

ፖሊስ በበኩሉ ገና ያልተሰበሰቡ ማስረጃዎችና ያልተቀበላቸው ምስክሮች እንዳሉ ጠቅሶ የዋስትና ጥያቄውን ተቃውሟል።

የጊዜ ቀጠሮ ጉዳን የተከታተሉት የችሎቱ ዳኞች ፖሊስ ከዚህ በፊት በተሰጠው ጊዜ የሰራውን ምርመራና አገኘሁ ያለውን የምርመራ ውጤት አስቀርበው ተመልክተዋል።

በዚህም መሰረት በርካታ የምርመራ ሥራ መስራቱንና ማስረጃ መሰብሰቡን መመልከታቸውን ጠቅሰዋል።

የምርመራ ሥራውን ውጤት ግምት ውስጥ በማስገባትና ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ አስፈላጊነቱን መታመኑን በመግለጽ ለፖሊስ ተጨማሪ 11 ቀን ምርመራ ጊዜ መፍቀዱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ከችሎት ዘግባለች።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች