መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናበኢትዮጵያ የአፍሪካ የጽሕፈት ሥርዓቶች ላይ ጥናትና ምርምር የሚያደርግ ቤተ ሙከራ ሊቋቋም መሆኑ...

በኢትዮጵያ የአፍሪካ የጽሕፈት ሥርዓቶች ላይ ጥናትና ምርምር የሚያደርግ ቤተ ሙከራ ሊቋቋም መሆኑ ተገለጸ

ሰኞ ነሐሴ 2 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የአፍሪካ የጽሕፈት ሥርዓቶች ላይ ጥናት እና ምርምር የሚያደርግ ቤተ ሙከራ ሊቋቋም መሆኑን የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተሌጀንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከቻይናው ሁዌዦንግ ዩኒቨርሲቲ ጋር አብሮ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

ሥምምነቱም የጋራ የምርምር ቤተ ሙከራ በማቋቋም ኢትዮጵያን የዘርፉ ማዕከል የማድረግ ዓላማ እንዳለው ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም በቴክስት ሪኮግኒሽን ቴክኖሎጂ ዙሪያ በቻይና እና አፍሪካ መካከል ትብብር እንዲኖር ያለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

እንዲሁም ሥምምነቱ የሰው ኃይል ልማት ትኩረት የተሰጠዉ ጉዳይ ሲሆን፤ በዚህም በትምህርት እና ቴክኖሎጂ ትብብር አብሮ ለመስራት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

የትብብር ሥራው በአፍሪካ የጽሕፈት ሥርዓቶች ላይ ጥናት እና ምርምር ለማድረግ የሚያስችል የጋራ የምርምር ቤተ ሙከራ በማቋቋም ኢትዮጵያን የዘርፉ ማዕከል የማድረግ ዓላማ እንዳለው ተመላክቷል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከሁዌዦንግ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር አፍሪካዊ ጽሑፎችን ከቴክኖሎጂ ጋር ለማግባባት የሚያስችለውን ዳታ የማልማት ተግባር እንደሚያከናውንም ተገልጿል፡፡

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች