መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናከደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ638 ሺሕ ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶች ተሠርቀው...

ከደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ638 ሺሕ ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶች ተሠርቀው ሊወጡ ሲሉ ተያዙ

ከአሁን በፊትም በሆስፒታሉ ሰራተኞች ከ6 መቶ ሺሕ ብር በላይ የሚገመቱ መድሃኒቶች መዘረፋቸው ተገልጿል

ማክሰኞ ነሐሴ 3 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በደሴ ከተማ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ638 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የህክምና ቁሳቁሶች ተሠርቀው ሊወጡ ሲሉ እጅ ከፋንጅ መያዙን የከተማው አስተዳደር ኮምዩኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል።

በሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር ሀይማኖት አየለ እንደገለፁት፤ ትናንት ነሐሴ 2 ቀን 2014 በግምት ከሌሊቱ 6 ሰዓት በሆስፒታሉ ውስጥ ግምታቸው ከ638 ሺሕ ብር በላይ የሚገመት የላብራቶሪ ማሽን፣ 4 ኦሎምፐስ (olomps) ማይክሮስኮፕ፣ 1 ላቦመድ (labomed) ማይክሮስኮፕ፣ 1 የኬሚስትሪ ማሽን(ዲያሚንሽን ማሽን ትንሿ ፕሪንተር፣ 1NEO-BIL የቢል ማሽን፣ 5 አዲስ ዶግለር የበር ቁልፍና የተለያዩ የኤሌትሪክ ገመድና ቁሳቁስ ይዞ ሊወጣ ሲል በጥበቃ ሰራተኞች እጅ ከፍንጅ ተይዟል።

ወንጀለኞችም በህገ ቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተካሄደበት መሆኑ ተገልጿል።

ከአሁን በፊትም በሆስፒታሉ ሰራተኞች ከ6 መቶ ሺሕ ብር በላይ የሚገመቱ ለክሮኒክ በሽታ የሚታዘዙ መድሀኒትና ሌሎች መድሀኒቶችም መበዝበሩን ዶ/ር ሀይማኖት አየለ ገልፀው፤ ዘረፋ ያካሄዱ 3 ሰራተኞች ከሥራ ተባረው በህግ እንዲጠየቁም ሲደረገ አንድ ባለሙያ ላይ ከደረጀ ዝቅ እንዲል ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

ሥራ አስኪያጇ አክለውም፤ የጥበቃ ሥራውን አጠናክረን ስንቀሳቀስ የሥርቆት ወንጀሉ ከውጭና ከውስጥ የተያያዘ ቁርኝት ያላቸው የሌብነት ሰንሰለት እንዳለ ተረድተናልና ህብረተሠቡ ሊያግዘንና ሊተባበረን ይገባል ብለዋል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች