የቡና ገለፈት ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያነት የሚቀይረው ፕሮጀክት ተመረቀ

0
481

የቡና ገለፈት ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያነት የሚቀይረው የምርምር ፕሮጀክት በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ተመረቀ። የምርምር ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት የስራ ኃላፊዎች ፣የደብረ ብረሃንና የዲላ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የፋብሪካ ተወካዮች እና የአካባቢው አርብቶ አደሮች በተገኙበት ተመርቆ ርክክብ ተደርጓል።

በኢትዮጵያ በባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ድጋፍ በደብረ ብረሃን ዩኒቨርሲቲ በተሰራው ምርምር በሲዳማ ዞን ሶስት ቀበሌዎች ላይ የምርምሩ ትግበራ እየተካሄደ መሆኑ ታዉቋል።

ምርምሩ በአካባቢው ቡና አምራቾች ችግር የሆነባቸውን የቡና ገለፈት በትሎች በማስበላት (በስነ ህይወታዊ ዘዴ) ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያነት በመቀየር ማስወገድ እንዳስቻለ ተገልጿል።

ምርምሩን ያካሄዱት ገዛኸኝ ደግፌ (ዶ/ር) ገለፈት ውሃን በመመረዝ በእንስሳት ላይም ጉዳት ሲያደርስ መቆየቱንና ምርምሩ ይህንን ችግር እንደፈታ ተናግረዋል።

የቡና ገለፈት ቡና የሚያመርቱ የአከባቢዉ አርሶ አደሮች ችግር ሆኖባቸው የቆየ ከመሆኑም ባሻገር መርዛማት ስላለው አካበቢውን ሲበክል እንደነበር የገለፁ ሲሆን በአሁን ሰዓት ግን ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያነት በሚቀይረው በዚህ ምርምር ስልጥነው የተደራጁ የአካበቢው ነዋሪዎችም የተፈጥሮ ማዳበሪያውን በመሸጥ ተጠቃሚ ሆነዋል።

የኢትዮጵያ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ካሳሁን ተስፋየ (ዶ/ር) ኢንስቲቲዩቱ በውጭ የሚከናወኑ 24 ችግር ፈቺ ምርምሮችን እየደገፈ እንደሆነና በቅርቡ ስምንቱ ተመርቀው ወደ ትግበራ እንደሚገቡ ተናግረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here