ዘምዘም ባንክ 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ አክሲዮኖችን ሸጠ

0
609

በምስረታ ከሚገኙት የኢስላሚክ ባንኮች መካከል አንዱ የሆነዉ ዘምዘም ባንክ  1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ አክሲዮኖችን ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ መሸጡን አስታወቀ። ስድስት መቶ ሚሊዮን ብር የሚያወጣው አክሲዮን የተከፈለ ሲሆን ቀሪው በቅርቡ ይከፈላል ተብሎ ይጠበቃል።

በጉዳዩ ላይ ዛሬ ጥቅምት 6/2012 መግለጫ የሰጠዉ የባንኩ መስራች ኮሚቴ  የአክሲዮን ሽያጩን እስከ ጥቅምት 15 እንደሚቆይ አስታዉቋል።

በናስር ዲኖ ሃሳብ አመንጪነት የዛሬ ስምንት ዓመታት በፊት ሊመሰረት ጫፍ ከደረሰ በኋላ ብሔራዊ ባንክ እስላሚክ ባንክ መመስረትን በማገዱ ምክንያት ምስረታው ለዓመታት ተቋርጦ የነበረው ዘምዘም ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ፈቃድ ማግኘቱ ይታወሳል።

ከዘምዘም በተጨማሪ በአሁን ወቅት ሶሰት የኢስላሚክ ባንኮች በምስረታ ላይ ሲሆኑ አክሲዮኖችን በመሸጥ ላይ ይገኛሉ።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here