በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት የተገነባው 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

0
1103

በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት አማካኝነት በጎንደር የተገነባው የሎዛ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዛሬ ጥቅምት 6/2012 ተመርቀ።

በ20 ሚሊዮን ብር ወጭ የተገነባው ትምህርት ቤቱን ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በይፋ በከፈቱበት ወቅት፤ የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የፌዴራል የትምህርት ዘርፍ አመራሮች እና ሌሎች እንግዶችም በምረቃው ሥነ ስርዓት ላይ ተገኝተዋል።

ትምህርት ቤቱ 28 የመማሪያ እና አራት የቤተ ሙከራ ክፍሎች፣ ቤተ መጻሕፍት እና የአስተዳደር ሕንጻ የተሟላለት ነው።

በቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት በአገሪቱ ከሚገነቡ 20 ኹለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል አራቱ በአማራ ክልል በጎንደር፣ ደባርቅ፣ ዋግ ኽምራ እና ደቡብ ወሎ ዞን እንደሚገነቡ ኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here