ሐሙስ ነሐሴ 12 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሀመድ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ ተብሎ የተሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ ሀሰተኛ ወሬ መሆኑን የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ።
የክልሉ መንግስት በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ “በትላንትናው ዕለት በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ሙሀመድ ላይ የግድያ ሙከራ ተደረገ ተብሎ የተሰራጨው ዜና ከእውነት የራቀ ሀሰተኛ ወሬ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን። ” ሲል ገልጿል።



