መነሻ ገጽዜናአቦል ዜናከእጥፍ በላይ ዓመታዊ ግብር ጭማሬ ተደርጎብናል ሲሉ የራይድና የፈረስ አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን ገለፁ

ከእጥፍ በላይ ዓመታዊ ግብር ጭማሬ ተደርጎብናል ሲሉ የራይድና የፈረስ አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን ገለፁ

ዓመታዊ ግብር ላይ ከእጥፍ ያላነሰ ጭማሬ ተደርጎብናል ሲሉ የራይድና የፈረስ አሽከርካሪዎች ቅሬታቸውን ለአዲስ ማለዳ ተናገሩ።

የራይድ እና የፈረስ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፣ በዘርፉ ወደ ሥራ ተሰማርተው አገልግሎት መስጠት ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ እንደማንኛውም የኮድ ሶስት ተሽከርካሪዎች ከስምንት እስከ ዘጠኝ ሺሕ ብር የሚደርስ በየዓመቱ ዓመታዊ ግብር ለመንግሥት ሲከፍሉ መቆየታቸውን አስታውቀዋል።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎቹ አክለውም፣ የገቢዎች ሚኒስቴር 2014 በጀት ዓመት በመደበኛው በኮድ ሶስት ግብር በምንከፍለው ላይ ተጨማሪ ጭማሬ በማድረግ ከ16 ሺሕ በላይ እንድንከፍል የተደረግንበት ሁኔታ አለ ብለዋል።

ገቢዎች ሚኒስቴር ለራይድ፣ ለፈረስ እና ሌሎች ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የግብር ተመን ከማስቀመጡ ቀደም ብሎ አሽከርካሪ ሰራተኞቻቸው በአንድ ዓመት ውስጥ ምን ያህል ኪሎሜትር የሚሸፍን የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደቻሉ እና በአንድ ዓመት ምን ያህል ገቢ እንዳስገቡ የማጣራት ሥራ አከናውነው ለግብር ከፋዮች ትእዛዝ እንደሚተላለፍ አሽከርካሪዎች ጠቁመዋል።

በተጨማሪ አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የራይድ፣ የፈረስን ጨምሮ ሌሎች የተሽከርካሪዎች ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ከአንድ እና ከኹለት ዓመት በፊት ከነበረው ሥራ አንፃር እንዲሁም ይገኝ ከነበረው ገቢ አኳያ መቀዛቅዝ እንዳሳየም ተናግረዋል።

አሽከርካሪዎች አክለውም፣ ለገቢዎች ሚኒስቴርም ሆነ ለሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ሮሮ ከማሰማት ባለፈ የግብር ጭማሬው የተመጣጠነ እንዲሆን እና አስተያየት እንዲደረግላቸው ቢጠይቁም፣ አጥጋቢ ምላሽ እንዳላገኙ ገልጸዋል።

አሽከርካሪዎቹ አያይዘውም፣ ከኹለት ወር በፊት የራይድ፣ የፈረስና የሌሎች ትራንስፖርት ሰጪዎች የታሪፍ መነሻ 65 ብር እንደነበር እና በአሁን ወቅት መነሻው 95 ብር እንዲሆን በድርጅቶቻችን እንደተወሰነ አስረድተዋል።

ይህ ደግሞ በአንድ ኪሎሜትር ርቀት እስካሁን ባለው ተሳፋሪዎቻቸውን 10 ብር ያስከፍል እንደነበር እና አሁን ላይ ወደ 13 ብር ከፍ ለማድረግ እንደተገደዱ ነው ያስረዱት።

ገቢያቸውን ከባለፉት ዓመታት ጋር ለማመጣጠን ጥረት ቢያደርጉም እንዳልቻሉ እና ገበያው ላይ ተፅዕኖ እያሳደረ መምጣቱን ነው የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ለአዲስ ማለዳ የጠቆሙት።

አክለውም፣ በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት ከፀጥታ አንፃር በተደራጁና ባልተደራጁ አካላትም ጭምር አንዳንድ ችግሮች እንደሚገጥሟቸውም አመላክተዋል።

በዚህ ሳቢያ ደግሞ አምሽተው የመሥራት እድላቸው ከመቀዛቀዙ እና የትራንስፖርት ተጠቃሚውም ቁጥር እየቀነሰ ከመምጣቱ ጋር ተደራርቦ ገበያቸው ቅናሽ እንዳሳየ ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር እንዲሁም በአዲስ አበባ ካለው የኑሮ ውድነት እና ከሌሎች ከተለያዩ ተደራራቢ ተፅዕኖዎች ጋር ችግራቸው የተደራረበ በመሆኑ መንግሥት ለጥያቄያቸው ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

አዲስ ማለዳ ስለጉዳዩ ለማጣራት ለገቢዎች ሚኒስቴር ያደረገችው ተደጋጋሚ ሙከራ ምላሽ ያላገኘ ሲሆን፣ ተቋሙ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ በሆነ ጊዜ የምናስተናግድ ይሆና


ቅጽ 4 ቁጥር 198 ነሐሴ 14 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች