10 ከፍተኛ የቻይና ዕዳ ያለባቸው የአፍሪካ አገራት

0
971

ምንጭ፡-AllAfrica

በርካታ የአፍሪካ አገራት ሊወጡት የማይችሉት እዳ ውስጥ የተዘፈቁ ስለመሆናቸው ይነገራል። በፈረንጆች 2021 ከቻይና ብቻ ከፍተኛ የዕዳ መጠን ያለባቸው የአፍሪካ አገራት ዝርዝር ይፋ በሆነበት ወቅትም የመጀመሪያዋ ከፍተኛ ተበዳሪ አፍሪካዊት አገር አንጎላ ሆናለች። እንደጥናቱ በ2021 አንጎላ 25 ቢሊዮን ዶላር የቻይና ዕዳ ተሸካሚ በመሆን ከአህጉሪቱ ቀዳሚ መሆኗ ታውቋል።

ኹለተኛና ሶስተኛ ሆነው የተቀመጡትም የምስራቅ አፍሪካ አገራቱ ኢትዮጵያና ኬንያ በቅደም ተከተል ናቸው። ከናይጄሪያና ጋና ቀጥሎ አስረኛዋ ከፍተኛ የቻይና ዕዳ ያለባት አገር ደግሞ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ነች።

ኢትዮጵያ ከቻይና ያለባት ዕዳ 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ይሁን እንጂ፣ በዚህ ወቅት ከአገር ውስጥና ከውጭ አበዳሪዎች አጠቃላይ 50 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ እንዳለባት ይታመናል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊት ኢትዮጵያ የነበረባት ዕዳ 28 ቢሊዮን ዶላር ገደማ መሆኑ ይነገራል።

ደርግ ከሥልጣን ሲወርድ ዘጠኝ ቢሊዮን ዶላር የነበረው የኢትዮጵያ ዕዳ በየዓመቱ በፍጥነት እያደገ ስለመሆኑም ነው የሚገለጸው።


ቅጽ 4 ቁጥር 198 ነሐሴ 14 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here