10 ከፍተኛ የምግብ ዋጋ ግሽበት የታየባቸው አገራት

0
1288

ምንጭ፡-የዓለም ባንክ (2022)

እንደ ዓለም ባንክ መረጃ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት በተለይ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባለቸው አገሮች ከፍተኛ የሆነ የምግብ ዋጋ ግሽበት ተከስቷል። በተለይ በሚያዚያ እና ግንቦት ወራት ግሽበቱ ከፍተኛ እንደነበር የተገለጸ ሲሆን፣ ዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ውስጥ ከኹለቱም በኩል 92 በመቶ በላይ በሚሆኑት ግሽበቱ ታይቷል። እንዲሁም ከበለጸጉ አገራት 89 በመቶ በሚሆኑት ይኼው የምግብ ዋጋ ግሽበት ተጋርጦባቸዋል።

በዚህ መሠረት ሊባኖስ ከፍተኛ የምግብ ዋጋ ግሽበት የተከሰተባት አገር ስትሆን፣ አፍሪካዊቷ አገር ዝምባቡዌም በ255 በመቶ ከፍተኛ የሆነ ግሽበት የታየባት አገር ሆናለች።

በኢትዮጵያም ከወትሮው በተለየ ሁኔታ የምግብ ዋጋ ግሽበት ያጋጠመ ሲሆን፣ እንደ ዓለም ባንክ መረጃም ከስምንት አገሮች ቀጥሎ በዘጠነኛ ደረጃ በዓለም የምግብ ዋጋ ቀውስ ውስጥ የገባች አገር ነች።

የሩስያና ዩክሬን ጦርነት፣ የምግብ ቁሳቁስ አቅርቦት ሰንሰለት ችግር እንዲሁም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በዓለም ዙሪያ ለተፈጠረው የምግብ ዋጋ ቀውስ እንደ ምክንያት ቀርበዋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 199 ነሐሴ 21 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here