መነሻ ገጽዜናአቦል ዜናበጋምቤላ ክልል በአንድ ቀን ብቻ ከ63 ሺሕ በላይ ዜጎች በጎርፍ አደጋ መፈናቀላቸው...

በጋምቤላ ክልል በአንድ ቀን ብቻ ከ63 ሺሕ በላይ ዜጎች በጎርፍ አደጋ መፈናቀላቸው ተነገረ

በጋምቤላ ክልል ከስምንት ወረዳ በአንድ ቀን ብቻ ከ63 ሺሕ በላይ ዜጎች በድንገተኛ የጎርፍ አደጋ መፈናቀላቸውን የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ።

የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት አደጋ ስጋት ሥራ አመራር አገልግሎት ኃላፊ ጋትቤል ሙን ለአዲስ ማለዳ እንዳሉት፣ በክልሉ በሚገኙ ስምንት ወረዳዎች ነሐሴ 18/2014 በአንድ ቀን ውስጥ ብቻ በተከሰተ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ 63 ሺሕ 970 የሚጠጉ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸው ለመፈናቀል ተገደዋል ብለዋል።

በክልሉ ከመጠን ያለፈ ጎርፍ ተከስቶ ዜጎች ለኹለተኛ ጊዜ እንደተፈናቀሉ እና አዲስ ማለዳ መረጃውን እስካጠናቀረችበት ጊዜ ድረስ የተፈናቃዮች ቁጥር ከ75 ሺሕ በላይ መድረሱን ከኃላፊው አረጋግጣለች።

ጋምቤላ ወረዳ፣ ጅሩ ወረዳ፣ አኮቦ ወረዳ፣ ወልታሮ ወረዳ፣ ጅካ ወረዳ፣ ላሬ ወረዳ እና በተጨማሪ ኹለት ወረዳዎች ላይ ድንገተኛ አደጋው የተከሰተ ሲሆን፣ በእነዚህ አካባቢዎች ከተጣለው ዝናብ በተጨማሪ በጋምቤላ ክልል አቅራቢያ ከሚገኙ የኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ቦታዎች ዘልቆ ወደ ክልሉ የገባው ጎርፍ ለአደጋው መንስኤ ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ሜትሮሎጂ ኢንስቲትዩት በክልሉ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ ሊከሰት እንደሚችል መጠቆሙን ተከትሎ፣ የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት የቅድመ ዝግጅት ሥራ ማከናወን የተቻለ ቢሆንም፣ ድንገተኛ የጎርፍ አደጋው ከታሰበው እና ከአቅም በላይ በመሆኑ ተፈናቃይ ዜጎችን መታደግ እንዳልተቻለ ኃላፊው ጠቅሰዋል።

ተፈናቃይ ዜጎችን ወደ ሌሎች ደረቃማ ናቸው ተብሎ ወደታሰቡ አካባቢዎች የማዘዋወር እና የማስፈር ሥራ መከናወኑን እና ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብዓዊ ድጋፎችን የማቅረብ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ኃላፊው አመልክተዋል።

የጎርፍ አደጋው በንብረትም ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን፣ ለአብነት ላሬ ወረዳ ብቻ በተደረገ ማጣራት ሂደት 386 የቁም ከብቶች፣ 1 ሺሕ 558 ፍየል፣ 179 በግ፣ 1 ሺሕ 226 ዶሮዎች መሞታቸውን እና በሌሎች ንብረቶችም ላይ ጉዳት መድረሱን ኃላፊው ተናግረዋል።

በተጨማሪ በሰባት ወረዳዎችም ተያያዥ የንብረት ጉዳቶች እንደተከሰተ እና የክልሉ መንግሥት የጉዳቶችን መረጃ በማጣራት ላይ መሆኑን ኃላፊው አመልክተዋል።

የክልሉ መንግሥት በቀጣይ በተጠቀሱትም ሆነ በሌሎች ቦታዎች አደጋ እንዳይከሰት በተቻለ አቅም የጥንቃቄ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው ብሏል።

በጋምቤላ ክልል ከአንድ ሳምንት በፊት በስድስት ወረዳዎች ላይ ተከስቶ በነበረው በመጀመሪያው የጎርፍ አደጋ እንዲሁ 11 ሺሕ የሚጠጉ ዜጎች ነበር ከአካባቢያቸው የተፈናቀሉት።

በክልሉ ባለፈው ዓመት እንዲሁ በደረሰ የጎርፍ አደጋ ከ13 ሺሕ በላይ ዜጎች በጎርፍ አደጋ መፈናቀላቸውም አይዘነጋም። ተከስቶ በነበረው የጎርፍ አደጋ የተፈናቀሉ ሰዎችን ለማቋቋም ከአቅሜ በላይ በመሆኑ ለፌዴራል መንግሥት ጥሪ ባቀርብም አፋጣኝ ምላሽ አላገኘሁም ማለቱም ይታወቃል።

ክልሉ ባለው አቅም በተወሰነ መልኩ የዘይትና የፉርኖ ዱቄት ድጋፍ ቢያደርግም፣ ድጋፉ ግን በቂ አልነበረም ተብሏል።

ለተፈናቃዮች ምንም ዓይነት መጠለያ እንዳልተሰራላቸው ተነግሮ የነበረ ሲሆን፣  ተፈናቃዮች በደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ መንገድ ዳር ላይ ተጠልለው የሚገኙ በመሆናቸው ዝናብም በሚዘንብበት ወቅት ከባድ ችግር


ቅጽ 4 ቁጥር 199 ነሐሴ 21 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች